ለእትሙ መግቢያ ያደረግነው የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ገላኔ ሌሊሳ የጽንስና ማህጸን ህክምና እስፔሻሊስት የነገሩንን ነው፡፡ በአለም ላይ ከ6 ጥንዶች አንዱ ልጅ መውለድ አይችልም፡፡ ልጅ የመውለድን ጸጋ ሁሉም የሚመኘው መሆኑን የዚህ እትም እንግዳ ዶ/ር ገላኔ በስእላዊ መግለጫ እንደሚከተለው አብራር ተውታል፡፡
‹‹…ቤተሰብ ሲመሰረት ፍቅርን ከመጋራት፤ኑሮን አብሮ ከማደርጀት ባለፈ ዘር መተካት የሚለውን ነገር ሁሉም የሚረዳውና የሚጠብቀው ነገር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ መካንነት ሲከሰት ከጥንዶቹ ጀምሮ ቤተሰብ እና ሌሎች ወገን ዘመዶች ሁሉ ያ ጥንድ ልጅ ባለመውለዱ ምክንያት ያዝናል፡፡ ትዳርም እስከመፍረስ ድረስ ይደርሳል፡፡ ነገር ግን ይህንን ማህበራዊ ጫና ወደ ጎን ትቶ ልጅ መውለድ ያልቻሉትን ጥንዶች ሁኔታ በቅጡ ማስተዋል ይገባል፡፡
መካን ያልሆነች ሴት ልጅ ከመውለድዋ በፊት በእርግዝናው ጊዜ የሚደረግላት እንክብካቤ፤ከአ መጋገቡ፤ከአለባበሱ፤ከህክምናው ክትትል፤ልጁን ከመናፈቅ፤ወልዳ በምትተኛበት ጊዜ በተ ረጋጋ ሁኔታ ልጁዋን እንድታሳድግ ለማድረግ ስለሚደረግላት እንክብካቤ በሁሉም መውለድ ባልቻሉት ቤተሰቦቸች ህሊና የሚመላለስ ነው፡፡ልጀ ከተወለደ በሁዋላ የሚኖረው ደስታ፤አብሮነት፤እንደ ክርስትና፤ልጅ ማስከተብ ፤ልደት መደገስ በመሳሰሉት ምክንያቶች በቤተሰብ ፤ወዳጅ ዘመድ ተከቦ ስርአቱን ማሳለፍ የመሳሰለው ሁሉ ባልወለዱ ሰዎች ዘንድ ለዚያ ያላቸውን ናፍቆትና አድናቆት መገመት አያዳግትም፡፡ ልጅ መውለድ ማህበራዊ ገጽታው…ማህበራዊ ውበቱ…ይና ፍቃል፡፡ ስለዚህም ልጅ መውለድ ካልተቻል አስፈላጊውን ሳይንሳዊ ዘዴ ሁሉ ለመተግበር በሀገር ደረጃ ትኩረትን የሚሻ ነው…..›› ብለዋል፡፡
ዶ/ር ገላኔ ወዳነሱት ጉዳይ ስናመራ የሚከተለውን ነበር ያብራሩት፡፡ የመካንነት ጉዳይ በብዙ ዎቻችን ዘንድ እንደህክምና ችግር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ነገር ግን በዋነኛነት የማህበራዊ ችግር ልንለው እንችላለን ብለዋል፡፡ ሴቶች ልጅ አለመውለድ በተፈጥሮም ሊያጋጥማቸው የሚችል
ነው፡፡ ምክንያቱም ተፈጥሮአዊው የእንቁላል ቁጥር የመቀነሱ ሂደት እንደ አንድ ምክንያት ሊቆጠር ስለሚችል ነው፡፡ ይህ ደግሞ በበሽታ ሁኔታም ጭምር የሚመጣ ሲሆን ነገር ግን ማህበራዊ እንደምታው በጣም ከፍተኛ ሆኖ ይገኛል፡፡ ልጅ አለመውለድ በተለይም እንደእኛ ሐገር ላሉ ባህል ለሚተኮርባቸው ፤የልጆች መወለድ በጣም ከፍተኛ የሆነ ዋጋ በሚሰጥባቸው ሐገሮች ያልወለዱ ጥንዶች ችግሩ ከወንድ ይሁን ከሴት ተለይቶ ሳይታወቅ ሴቶቹ ላይ በጣም ከፍተኛ የሆነ ተጽእኖ ያድርባቸዋል፡፡ ዶ/ር ገላኔ እንዳብራሩት የመካንነት ሁኔታ ባህላዊ አስተሳሰባቸው ፤እምነታቸው፤ልማዳቸው ባልዳበረባቸው ሀገራት ከፍተኛ የማህበራዊ ቸግር ተደርጎ ከመወሰዱ የተነሳ የተለያዩ ባህላዊ፤ሀይማኖታዊ፤ልማዳዊ ነገሮችን በመከወን የቻሉትን ሲያደርጉ መቆየታቸውንና አሁንም ቢሆን በአንዳንድ ሀገራት ድርጊቱ ይፈጸም ይሆናል የሚል እምነት አለ፡፡ ስለዚህ ተመራማሪዎች ከህክምና ችግርነቱ ይልቅ ማህበራዊ ችግርነቱ ያደላል ብለዋል፡፡ በእርግጥ በህክምናው ዘርፍ የተለያዩ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም መውለድ ላልቻሉ ጥንዶች መፍትሔ መስጠት ከተጀ መረ ቆይቶአል፡፡ በአጠቃላይ ግን ልጅ አለመውለድ በተለይ ለሴቶች እንደእኛ ባሉ ሀገራት ማህበራዊ፤ስነልቡናዊ፤ኢኮኖሚያው ችግር ነው፡፡
ዶ/ር ገላኔ ወደሁዋላ ተመልሰው ሁኔታውን ሲያስታውሱ እንደሚከተለው ነበር የያብራሩት፡፡ ከዛሬ 50/አመት ገደማ ጀምሮ ጥንዶች ልጅ መውለድ በሚፈልጉበት ጊዜ የሚያስፈልጉት በጣም መሰረታዊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት የማይችሉበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ለምሳሌም በሴት በኩል መኖር ያለበት እንቁላል፤በወንድ በኩል መኖር ያለበት የዘር ፍሬ በምንም አይነት ሁኔታ የማይገኝባቸው አጋጣሚዎች ይከሰታሉ፡፡ ይህም በተፈጥሮአዊ ሁኔታ ወይንም በተለያዩ የጤና እክሎች (በኦፕራሲዮን፤በካንሰር ሕክምና…ወዘተ) ምክንያት የተከሰተ ሊሆን ይችላል፡፡ይህ ጉዳት በተከሰተባቸው ጥንዶች በኩል የራሳቸው የሆነ የዘር ክፋይ ሊኖር አይችልም፡፡ በእርግጥ በዚህ ጉዳይ ጥናት እየተደረገ ነው፡፡ ይህ ጥናትም ከሌሎች ሴሎች የዘር ፍሬ ለማምረት ይቻላል ወይ የሚለው ጥናት እየተደረገ ነው፡፡ ይህ በሌለበት ሁኔታ መጠየቅ የሚገባን ሰዎች ምን ሊመርጡ ይችላሉ ? ምን እየመረጡ ነው? በአለም ላይ ምን እየተተገበረ ነው? የሚለውን ነው፡፡
ዶ/ር ገላኔ እንደገለጹት ሰዎች በአለማችን በተለያዩ ሀገራት የዘር ፍሬ እና እንቁላል ከሚታ ወቁም ይሁን ከማይታወቁ ሰዎች በልግስና የሚገኘው ተወስዶ በላቦራቶሪ እገዛ ለዚያ ጥንድ ጽንስ ይሰራል፡፡ ከዚያም ወደ እናትየው (መውለድ ወዳቃታት) ማህጸን እንዲገባ ተደርጎ ልጁ አድጎ እንዲወለድ ይደረጋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ልገሳው ልጅን በማህጸን ተሸክሞ አሳድጎ የሚወልድ ሰው ፍለጋ ሊሆን ይችላል፡፡ የሴትዋ ማህጸን ልጅ መሸከምና ማሳደግ በማይችልበት ጊዜ ከእራስዋ እንቁላል እና ከባለቤትዋ የዘር ፍሬ ተወስዶ በላቦራቶሪ እንዲጸነስ ከተደረገ በሁ ዋላ በልገሳ ወደተገኘው ማህጸን ገብቶ ልጅ እንዲወለድ ማድረግም ይቻላል፡፡ በእርግጥ ለጋሾ ችም ይሁኑ ተቀባዮች ስነልቡናዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ አንዳንድ ጊዜ ማህጸን የለገሱም ሁኑ የዘር ፍሬና እንቁላል የለገሱት ሰዎች የታወቁ በሚሆኑበት ጊዜ የተ ወለደው ልጅ የእኔ ነው ወደሚለው ዝንባሌ እንዳይሄዱ ነው፡፡ በሌላም በኩል ይህ ሁኔታ የተ ወለዱትን ልጆችም ሊነካ ይችላል፡፡ እኔ በትክክል ዝርያዬ ከማን ነው ? የማን ልጅ ነኝ? ብለው የመጠየቅ መብታቸውን በሚያስከብሩበት ጊዜ ቤተሰባዊ ሁኔታው ላይ ጫና ያሳ ድራል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የማህጸን ኪራይን በሚመለከትም የተረገዘው ልጅ ሲወለድ ምናል ባት ተፈጥሮዊ ችግር ቢኖርበት እነዚያ ወላጅ እንዲሆኑ የታሰቡ መካን ጥንዶች ይህንንማ አንረከብም…ይሄ የእኛ ልጅ አይደለም በማለት እንቁላልና የዘርፍሬ አዋጥተው የተረገዘላቸውን እና የተወለደውን ልጃቸውን ጥለው ከሀገር እስከ ሚሰደዱ ድረስ እርምጃ ይወስዳሉ፡፡ ስለዚ ህም የተመረጠው በአለም ላይ በአብዛኛው ከማይታ ወቁ ሰዎች ልገሳን መውሰድ ነው፡፡ በእ ርግጥ እነዛ ሰዎች በአሰራር ደረጃ አይታወቁም ማለት አይደለም፡፡ ማንነታቸው ተመዝግቦ ስርአቱ እንዲካሄድ ይደረጋል፡፡ በግል ግን እንቁላሉ የእከሌ ነው…የዘርፍሬው የእከሌ ነው ተብሎ እንዲለገስ አይደረግም፡፡ የማህጸን ኪራዩም ቢሆን የማንን ልጅ እንዳረገዘች ሳታውቅ በአሰራር የሚፈጸም ይሆናል፡፡
በተለያዩ ሐገራት ይህንን አሰራር በሚመለከት ዝርዝር መመሪያና ህግ ወጥቶላቸው በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ አንድ ልጅ የማን ልጅ ነኝ ብሎ ቢጠይቅ እንዲነገረው የሚያስችል፤አንድ ለጋሽ ለስንት ሰው ይለግስ ወይንም ትለግስ ለሚለው ሁሉ ዝርዝር መመሪያ አውጥተው ጠቀማሉ፡፡
አንዳንድ ጊዜ የዘር ፍሬም ሆነ እንቁላል መለገስ የሚያስደስታቸው ሰዎች ዝም ብለው ቢለግሱ መጨረሻ ላይ ስለማይተዋወቁ እና ቀጥሩም ከአንድ ለጋሽ የተገኙ እስከ 100( አንድ መቶ )ልጆች ሊደርሱ ቢችሉ እርስ በእርሳቸው ሁሉ ሊጋቡ የሚችሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ ይህ ችግር እንዲከሰት ስለማ ይፈለግ አንድ ለጋሽ ሴትም ትሁን ወንድ ውስን በሆነ ደረጃ እንዲያውም አንድ ለጋሽ ለአንድ ጥንድ በሚል ተገድቦ የሚያዝበት ሁኔታ ያለባቸው ሐገራት አሉ፡፡ ዶ/ር ገላኔ እንዳሉት በዓለም ላይ ከስድስት ጥንዶች አንዱ ጥንድ ልጅ መውለድ አይችልም፡፡ በማህበራዊው አመለካከት ችግሩን በመረዳት በእነዚህ ልጅ ማግኘት ባልቻሉ ጥንዶች እግር ቆሞ መመልከት የማይቻልባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው፡፡ አላስፈላጊ የሆኑ አሰተያየቶችም ሲሰጡ ይሰማል፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ተገቢ የሆነ ምክር ከመለገስ ይልቅ ልጅ ባለመውለዳቸው ምክንያት እንዲከፉ የሚያደርጉ አሉ፡፡ ስለዚህም ሳይንስ እነዚህ ጥንዶች እንደማንኛውም ጥንዶች ልጅ ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ የቀየሰ ሲሆን በተሻለ መንገድ ለመከወንም ሰፋ ያሉ ጥናቶች እየተካሄዱ ነው፡፡ ወደሀገራችን ኢትዮጵያ መለስ ብለን ስንመለከት ብዙ የአፈጻጸም መመሪያዎችን እንደሚጠይቅ እሙን ነው፡፡ የሚለግሱት ሰዎችም ጤንነታቸው፤የወደፊት የስነተዋልዶ ህይወታቸው በደንብ መጤንና እንዳይጎዳ የሚያደርግ አሰራር መዘርጋት አለበት፡፡ ጤንነታቸውም በሚገባ የተጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ አሰራሮች ሊኖሩ ይገባል፡፡ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የህክምና ስነምግባርን ባማከለ ሁኔታ ሊሰራ የሚገባው ነው ብለዋል ዶ/ር ገላኔ፡፡ ዶ/ር ገላኔ ሌሊሳ አክለ ውም ህብረተሰቡም ቢሆን እንደ እንቁላል እና የዘር ፍሬ ለጋሽም ፤ተቀባይም ወንዶችና ሴቶች ሆኖ ሊያስብበት ይገባል፡፡
ከስድስት ጥንዶች በአንዱ የመካንነት ችግር ይስተዋላል ሲባል እስከ አስራ አምስትና ሀያ ከመቶ የሚደርስ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ችግር መሆኑ አይካድም፡፡ እነዚህ ሰዎች ቀና ብለው በአደባባይም ይሁን በህብረተሰቡ መካከል ለመናገር እንኩዋን አይደፍሩም፡፡ በእራሳቸው ፍላጎት እና ምርጫ መካንነት የመጣ ይመስል ተሸማቀው፤ሳይደሰቱ ህይወታቸውን የሚገፉ ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሊደረስላቸው ይገባል፡፡ በስተመጨረሻም ዶ/ር ገላኔ ሌሊሳ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት አሁን በኢትዮጵያ በመሰጠት ላይ ያለው የ IVF ህክምናም (ጽንስን በላቦራቶሪ መፍጠር) ሰፋ ባለ መልኩና ዋጋው ተመጣጣኝ በሆነ መንገድ ቢሰጥ፤እንዲሁም የዘ ርፍሬ ፤የእንቁላል ልገሳው እና የማህጸን ኪራዩ ጉዳይ በህግ ተደግፎ አሰራሩ የሚዘረጋበት መን ገድ በአፋጣኝ ቢፈለግ ልጅ ላጡ ወገኖች መድ ረስ ይቻላል ብለዋል፡፡
Saturday, 28 September 2024 20:19
Published in
ላንተና ላንቺ