Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 31 December 2011 09:21

“ቃል የእምነት እዳ እንጂ የእናት አባት ውርስ አይደለም፡፡”

Written by 
Rate this item
(3 votes)

“ያፈቀረ ልብ ይህንን አስፀያፊና ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት አይፈጽምም”

የኤቢን እህት  ሳላገናኝ ለረጅም ዓመት አብረን ያሳለፍን አብረን የኖርን ጓደኛ የነበረችኝ ሲሆን ድንገት በተፈጠረው የኢትዮ ኤርትራ ፀብና ጦርነት ምክንያት ሳንወድ በግድ ልንለያይ ችለናል፡፡ ሆኖም ግን አንድ ቀን እግዚአብሔር የፈቀደለት እንደምንገናኝ  ስለት ነበረብን የሚገርመው ለኤቢ ቀለበት ባረኩላት በነጋታው የቀድሞ ጓደኛዬ ደውላ በጣም እንደምትፈልገኝ ስትነግረኝ የምትፈልገኝ ለምን እንደሆነ በስልክ እንድትነግረኝ ብጠይቃት በስልክ እንደማይቻል ስትነግረኝ በአካል እኔ ቤት እንድንገናኝ ተቀጣጥረን ስንገናኝ የሚያሳዝና የሚያስደነግጥ ነገር ነገረችኝ፡፡

እርሱም ከአሁን በኋላ አብረን እንኑር ልጆችም እንወልዳለን፡፡ ድሮውንም አንተ ትወደኛለህ እኔም እንደምወድህ ታውቃለህ፡፡ ስለዚህ በሥርዓቱ ተጋብተን እንኑር አለችኝ፡፡ በወቅቱ ላስብበት ብያት ተለያየን፡፡ በመጀመሪያም ቀጥታ ወደ ቤተክርስቲያን ነው የሄድኩት፡፡ ከዛም ከአምላክ ጋር አምላኬ ምንድነው እያደረከኝ ያለኸው ምን አረኩ ብዬ ምርር ብዬ አለቀስኩ፡፡ ስጠብቀው የነበረ ነገር ያውም በትልቅ ተስፋ ሲሳካልኝ ለምን ምርር ብዬ እንዳለቀስኩ ለኤቢ የቃል ኪዳን ቀለበት ስላደረኩኝ የቀድሞ ዋን ጐደኛዬን እሺ ማለት ኤቢን መካድ መስሎ ተሰማኝ እንቢ እንዳልላት ፍቅር አለብኝ ልጅም ወዲያው ስወልድ ተሰማኝ፡፡ በመሀል ለመወሰን ተሰቃየሁ፡፡ ከዛ ግን የግድ መወሰን ነበረብኝ፡፡ እናም አውጥቼ በማውረድ ውሳኔ ላይ ደረስኩ፡፡ ውሳኔዬም ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታማኝ ልሁን በሚል (ለኤቢ ታማኝ ልሁን) አልኩኝ የቀድሞ ፍቅረኛዬም ልትወልድልኝ ያሰበችውንም ልጅ ጭምር ትቼ ቃል ኪዳን ተስፋ ኤቢን አስበልጬ እርሷ ጋር ሆንኩኝ፡፡ኤቢ በሀሰት የሽንገላ ቃልሽ ተታልዬ እና ያሰብሽውን ሥውር ህልምሽን ለማሳካት ስትይ “ፊሽ እኔ ያልተማርኩ መሀይም ወይም ህፃን ልጅ አይደለሁም ባይገርምህ አሰልቺና ረጅም እድሜ ከመኖር አጭር አስደሳች ጊዜ ካንተ ከምወድህና ከማፈቅርህ ጋር መኖር ምርጫዬ ነው” ያልሽውን አንቺ እንደምታስቢው ጅል ወይም ሞኝ ሳልሆን ለፍቅርየተከፈለ መስዋት መስሎኝ ከእግዚአብሔር የተሰጠሽኝ ስጋዬና ፍቅረኛዬ ባጠቃላይ ለእኔ ሁሌም ነገሬ ሆነሽ እድሜዬን፣ ገንዘቤን፣ ማንነቴን ሁሉም ነገሬን አሳልፌ መስጠቴ እኔ ከHIV ጋር አብሬ እንደመኖሬ ያንቺ መስዋትነት ከምንም በላይ እንደሆነ አድርጌ እቆጥረው ነበር፡፡ ይህን ግን ስህተቴና እራሴን ከማወቄ በላይ አንቺን አውቃለሁ ብዬ አስብ ስለነበር ነው፡፡ ኤቢ ባይገርምሽ ይህ ችግር ተከስቶ ባይሆንና አንቺም እኔን በሀሰት ቃልሽ እየሸነገልሽኝ እኔ ደግሞ ለፍቅሬ የቀረችኝን እድሜ መስዋት እየከፈልኩ ህይወቴ ብታልፍ ደስታዬ ነበር፡፡ ኤቢ አሁን ይህን ሁሉ ልተነፍስ የቻልኩት የአጐትሽ እናየ እህትሽ በህዝብ ዘንድ የሀሰትና የአውሬነት ባህሪ እንዳለኝ ስዕል ስለሰጡኝ አይደለም ቢያንስ አንቺ ሁሉንም ነገር ለህሊናሽ ትመሰክሪያለሽ በሚል ብቻ ነው፡፡

ይህንንም በችሎት ቀርበሽ እውነትን እስክትተነፍሽ እጠብቅ ነበር አልሆነም፡፡ ኤቢ እስቲ አሁን ባለሽበት ቦታ እኔ ላንቺ የከፈልኩትን መስዋዕት አስቢው አንቺንስ ልጐዳ የሚችል ልብስ ነበረኝ ወይ? እኔ ላንቺ ስል ልጄን የአብራኬ ክፋይ የሆነችውን እኔን ወይም ልጅህን ምረጥ ስትይኝ አንቺን መርጫለሁ፡፡ እንዲሁም እናቴ ከአገር ቤት በህመም ምክንያት መጥታ ህክምናዋን ሳትጨርስና ሳትድን ልኬያት እሷንም ቢሆን አጥቻታለሁ፡፡ ኤቢ ላንቺ ምቾት ስል እህቴ ከኮረም እኔ ጋር በህመም ምክንያት ቤቴ መተኛ አልጋ የለም ብዬ ሆቴል እንዳሳደርኳት አንቺ ታውቂያለሽ፡፡ ነገር ግን ኤቢ ያንቺ ቤተሰቦችና ዘመዶች እኔ ጋር መጥተው ሲያርፉ በፍቅር አስተናግጃለሁ፡፡ የእኔን ቤተሰቦች ዞር ብዬ ሳላይ ለአንቺ የገጠር ዘመዶች በሬ መግዣ ብር መላኬ እንዲሁም ለእህትሽ ሔርሞን ሀይላይ የኮንዶሚኒየም ቤት ከመግዛት ባለፈ የቤቴን ካርታ በማስያዝ ብድር (ገንዘብ) እንድታገኝ በማድረግ በመኖሪያ ቤቴ በወር እስከ 2000 ብር የሚከራይ ውስጥ የኮስሞቲክስ መሸጫ ሱቅ ከፍታ እንድትሠራ ማድረጌ (አሁንም በቤቱ እየሠራች ትገኛለች) ኤቢ በዙሪያዋ ምንም እንዳታሰብና እርሷ ለእኔ ልትከፍል ከተዘጋጀችው ከነበረው አንፃር የሚታሰብ አይደለም፡፡ ኤቢ አንቺ ሁሉንም ታውቂያለሽ የፀረ HIV  መድሀኒት ተጠቃሚ ብሆንም አንቺ ሳትመጪ እና ከመጣሽም ብቻሽን መብላት የለብሽም ከሚል መድሀኒቱን በባዶ ሆዴ እውጠው ወይም ደግሞ ሰዓቱን አሳልፌ እንደምውጥ ታውቂያለሽ ከዚህም አልፎ በዚህ በሽታ ተይዤ ካንቺ ምንም ሳልደብቅ እና ለ10 ዓመት አብሬሽ ስኖር አንቺ ከምታደርጊው ጥንቃቄ በላይ እኔ ላንቺ ምን ዓይነት እንደነበርኩ ከእኔ በላይ ላንቺ ስኖር እንደነበር ታውቂያለሽ፡፡ ኤቢ እኔ እኮ በበሽታው ብያዝም አንቺ ባለመያዝሽ ከአንቺ በላይ መደሰቴንና ከዛም በኋላ የህይወት ጐዳናችንን በተመለከተ አንቺን ነፃ አድርጌ እንድትወስኚ ማድረጌ እና እንዳላስቸግርሽ የግዴን ለመሸሽ ብሞክርም አንቺ ግን ተከታትለሽኝ በመጥራት እኔ አንቺና እግዚአብሔር ባለበት እንደምትወጂኝ፣ አብረሽኝም በጋብቻ ተሳስረን እንደምትኖሪና ረጅም አሰልቺ ህይወት ከመኖር አጭር አስደሳች ህይወት መኖር እንደምትፈልጊ ከመግለጽሽም በላይ ትንከባከቢኝና ታዝኝልኝ ቢሆንም ይህ ግን በዝች ዓለም ቆይታው ትንሽ ነው ሲሞትም ወርሰሽ ለመኖር እቅድሽን ሳስብ ይገርመኛል፡፡ ምክንያቱም እኔ ከእርሷ ጋር መኖር ከጀመርኩ በኋላ እና HIV በደሜ መኖሩን ካወኩ በኋላ ለጤናዬ እንክብካቤ በማድረግ በቤቴ የእስፖርት ጂም በማስገባት በጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘቴ እና የእርሷም እድሜ እየጨመረ መሄዱን ስታስብ የእኔ ከዚህ አለም መሠናበቻ እየረዘመ መምጣት በአንቺ ዘንድ ጥሩ አለመሆንና የነበረሽን ባህሪ በመቀያየር የእኔ ሰላምና ጤና እንዲናጋ ማድረግሽን ሳስብ በጣም ይገርመኛል፡፡ መዝናናት ቢያምረኝ የእርሷ ፍቃድና ካልፈለገች አለማድረጌ ዘወትርም የአንቺን ስሜትና ፍላጐት ስጠብቅና ስንከባከብ መኖሬ ለፍቅሬ ስለሆነ ሁሌም ከመከፋት ይልቅ እደሰት ነበር፡፡ በጊዜ ሂደት ለእራሷ፣ ለእግዚአብሔር እና ለእኔ የገባችውን ቃል ትታ ድብቁን አላማዋን ለማሳካት መንደርደር ስትጀምር ከዚህ በፊት ልጅ ወልደን ስንኖርና በልጆቻችንም ስም ማውጣት ላይ ይህ ስም ለልጄ አይሆንም ይህ መሆን አለበት እየተባባል ስንነጋገር የነበረውን እረስታ ከእንግዲህ ልጅ መውለድ እንደማትፈልግ ከእኔ ጋር በመሆኗም በበሽታው እንድትያዝ አለመፈጓን እና ንቀቷን ሳይ ለ10 ዓመት አብረን ስንኖር ከእርሷ ይልቅ እኔ ለእርሷ ብዙ ጥንቃቄ የማደርግ እና እስከ ዛሬም እንዳትያዝ ያደረኩትን መዘንጋቷ ቢገርመኝም እኔ ግን ለእርሷ የማያልቅና ጥልቅ የፍቅር ስሜት ያለኝ በመሆኑ አልከፋም፡፡ በወቅቱም ያሰበችው ፍላጐት በአጭር አለመሳካቱን ስታውቅ የእኔን ስሜት ከመጉዳት ባለፈ ፀባዩ ተቀያይሮ እስከ ፍቺ የሚያስገባ ሁኔታ ቢፈጠርም እኔ ግን ካለብኝ በሽታ ተደምሮ እና በበሽታውም ምክንያት የምወዳትንና የማፈቅራትን ልጅ ስነጠቅ ከዚህ በፊት ስለ በሽታው ተሰምቶኝ የማያውቀው ስሜት ቢሰማኝም በእምነት እንደምድንና እርሷንም ማግኘት እንደምችል በማሰብ ፀበል በመሄድ እጠመቅና እፀልይም ነበር፡፡ በሰዓቱም ህመሙ በርትቶብኝ መንፈሴም አካሌም በጣም ታወከ፡፡ በስተጨመረሻ በህክምና እርዳታ ከበሽታዬ ከማገገሜም በላይ በእርሷ ምክንያት ትዳሬን ከማፍረሴም በላይ እርሷን ከማግኘቴ በፊት እና በኋላ ያፈራሁትን ንብረት ማለትም በእኔና በእርሷ ስም የገዛሁትን 2 አክሲዮን (የ4 ሚሊዮን ዋጋ ያለውን) ለመኖሪያ የሚሆን የገዛሁትንም ቦታ በተመለከተ በፍርድ ቤት እንድንካፈል አድርጌም እስከዛሬ ድረስ ለእርሷ ከእምነቴ በስተቀር ሁሉንም ነገሬን (ጊዜዬን፣ ገንዘቤን…) መስዋት አድርጌ ምንም ሳልበድላት በእርሷ የማይረባ ምክንያት ለእዚህ በመብቃቴ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስንለያይ “ኤቢ እድሜን ሁሉ ከአንቺ ጋር ሆኜ ጨርሸዋለሁ አንቺ ክህደት ፈጽመሽብኛል እኔ ግን ይቅርታ አድግጌልሻለሁ በሚል የተለያየን ቢሆን፡፡ እርሷ ግን ሁሌም ትከታተለኝ ስለነበር በስነ - አእምሮ በመጐዳቴ የሳይካትሪስት ባለሙያ ጋር ህመሜን እያስታመምኩ በነበረበት ሰዓት ያለሁበት ቦታ ድረስ እየተመላለሰች ታገኘኝ ጀመር፡፡ሌላው የኤቢ ቤተሰቦች እናቷ፣ እህቶቿ እንዲሁም አጐቷ መልካም ግንኙነት ያለኝ በተለይ ከአጐቷ ጋር በእርሷ ምክንያት ትንሽ ቅሬታ ያለኝ ቢሆንም እናቷ ይህ ድንገተኛ አጋጣሚ እስከተፈጠረና እኔም እስር ቤት እስከመግባቴ ድረስ አብራኝ የምትኖር ሲሆን ለትንሿ የኤቢ እህት ኤቢ ለልጅቷ ወራዊ ተቆራጭ በማቋረጧ እኔ የምረዳት ሲሆን ሌላዋ ታናሽ እህትም በእኔ መኖሪያ ቤት የንግድ ሥራዋን ለእራሷ እየፈፀመች ትገኛለች፡፡ ምንም እንኳን የእኔን መጥፎነትና ጨካኝነት በማጉላት የኢትዮጵያ ህዝብን ወደተለየ አቅጣጫ እንዲሄድ ማድረጋቸው ውስጤን ቢጐዳውም እኔ ግን ለእነርሱ የሆንኩትና ያለውን እውነት በመካድ እንደዚህ ቢያደርጉም እኔ ግን ለእነሱ ያለኝ ከበሬታና ፍቅር አይቀየርም፡፡በስተጨመረሻ ከአመት በዓል (በ2004 ዓ.ም) አዲስ ዓመት በማግስቱ አጐቷ ቤት የምሳ ግብዣ ተደርጐልን በቦታው ተገኝተን ያለውን ምግብና መጠጥ ቀምሰን እርሷም ወደ ፀጉር ቤት ልሠራ ልሂድ ብላ ስትሄድ እኔም ከእዛ ወጥቼ ለብቻዬ መጠጥ ቤት መጠጣት የጀመርኩ ሲሆን፤ ነገር ግን ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ሸራተን ከሰው ጋር ተቀጣጥሬ የነበረ በመሆኑ እና ወደ እዛው በመሄድ ላይ እያለሁ የኤቢ ስልክ አቃጨለብኝና አነሳሁት፡፡ ሳናግራት የምሄድበትን ፕሮግራም አስትታ እቤት እንድመጣና እንደምትፈልገኝ ስትነግረኝ ወደ እርሷ ቤት በመሄድ መድረሴን በመግለጽ እንድትከፍትልኝ ስነግራት ከፍታልኝ እቤት ገብቼ የሚጠጣ አቅርባልኝ ሁለታችንም እየጠጣን በነበረበት ሰዓት እኔ ከዚህ በፊት ለታናሽ እህቷ አጫውቻት የነበረውን ሁኔታ ማለትም ከኤቢ ጋር በአንድ ላይ መኖር ስለማልችል እና ከእኔው ጋር በደም ውስጥ የHIV ቫይረሥ ያለባትን ጥሩ ልጅ ማግኘቴና ከእርሷ ጋርም ለመኖር እየተዘጋጀሁ መሆኔን ከታናሽ እህቷ ጋር ሥለምንወያይ ሁኔታውን ለእርሷ በመንገሬ እህቷ ደግሞ ለኤቢ በመንገር ኤቢ ደግሞ ይህ ሁኔታ ሲቆረቁራት ኖሮ ለካ ከ4፡00 ሰዓት አሥጠርታኝ በነገር እየነካካችኝ “ከእኔ የተሻለች ሴት የት ነው ያገኘኸው?”  ደግሞ ይህንን ማን ነገረሽ በሽተኛ ሴት ደግሞ ከእኔ በምንድን ነው የምትሻለው? ሥትለኝ ኤቢ እንዴ ምን እያልሽ ነው በሽተኛ የምትይው ሥላት” ወደ መኝታ ቤቷ በመግባት ሽጉጥ አውጥታ እኔ ላይ ደቀነችብኝ እንዴ ኤቢ እየቀለድሽ ነው ወይስ አውቀሽ ስላት ዝም በል እንዳላንበረክክህ ሥትለኝ ለምን ተኩሰሽ አትገድይኝም ስላት በሽተኛና የሞተን ሰው ተኩሼ አልገልም፡፡ አንተ already የሞትክ አይደለህም ስትለኝ እኔም ከጠጣሁት መጠጥ ጋር እና ከኤቢ ንግግር ጋር ተደበላልቆ እየተናደድኩ መጣሁ እርሷም የምሯን መሆኑን ከመረዳቴም በላይ በተደጋጋሚ በሽተኛ ከበሽተኛ ጋር ተገናኘ አልተገናኘ ከጤነኛ ጋር እንዴት ነው የሚወዳደረውና የሚሻለው እቤቷ ጠርታኝ እንዲህ ውስጤን ሥትጐዳውና እንደ ውሻ ሥታደርገኝ እና በሽጉጥ ደቅና እንድወጣ ስትለኝ ድንገት በማላቀው ሁኔታ ሽጉጧን ከእጇ ላይ በማስጣል ግብ ግብ ተያይዘን ወደቅን ከዛ በኋላ የሆነውን የማላውቅና በስተመጨረሻ ሥነቃ እርሷ ከላይ እኔ ከስር የነበርኩ ሲሆን እርሷን ገልብጬ በሁኔታው እጅግ በመፀፀት ቆም ብዬ “ኤቢ ጉድ አደረግሽኝ፣ ወይኔ እግዚአብሔርዬ እያልኩ” ሳለቅስ ከቆየሁ በኋላ ወዲያው ሥልክ ደውዬ የሚረዳን ሠው ሥፈልግ የኤቢን ድምፅ ሰማሁ “ፊሽ በረደኝ አልብሰኝ ሥትል” እርሷንም አልብሼ ስልክ ደውዬ የሚረዳን ሰው አጣሁ ሊረዳኝ የሚችል ስልክ ካለሽ ስላት የ97 ሥትለኝ ሥደውል እነርሱም የ94 እንድደውል ሲሠጡኝ ብደውልም የሚመልሥልኝ የለም ኤቢን የሚረዳ ሰው ሥላጣሁ ፖሊስና ሀኪም ይዤ እመጣለሁ ብያት ልወጣ ሥል ፍራሽ ላይ አሥተኛኝ አለችኝ አሥተኛኋት ልብሰ ደርብልኝ ብላኝ ደረብኩላትና ድንገት የሚረዳት ሰው ከመጣ መኝታ ቤቷ ወርቅና ገንዘብ ሥለነበር መኝታቤቷን ቆልፌ የዋናውን ቤት እርሷ ያለችበትን ገርበብ አድርጌ ፖሊሥ ጣቢያ ሔድኩኝ በወቅቱም ጣቢያ ውስጥ እሳት አንድደው ለመሞቅ እየተዘጋጀ በመሆኑና ከቀድሞ ባለቤቴ ጋር ችግር እንደተፈጠረ እና አሁን እርዳታ እንደሚያስፈልጋት ነግሬ ቶሎ እንዲሔዱ እና በመኪናዬ ጭኜ ኤቢ ጋር አደረሥኳቸው፡፡ ኤቢ ብዬ ስጠራት አቤት ሥትለኝ በዚህ ጊዜ ፖሊሶች እኔ ውጪ እንድወጣ አድርገው ሁኔታውን ካዩ በኋላ ህክምና ትሒድ እኔ አሳክማታለሁ አልኩና አብሬ ወደ ኮሪያ ሆስፒታል ወሠድኳትና ያሳከምኳት ቢሆንም እኝህ የተባረኩ ሼክ አላሙዲ ወደ ውጪ ወሥደዋት ባያሳክምዋት ኖሮ ያለኝን ንብረት ሸጬም ቢሆን ማሳከሜ አይቀርም ነበር፡፡ ከዛ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱኝና መርማሪ ፖሊስና አባዲናም በመያዝ ኤቢ ቤት በመሔድ አሻራ ተነሳ የተሠባበረ ሽጉጥ፣ መጠጥ፣ ጐራዴ፣ … የተለያዩ ነገሮችን ፎቶ አነሱ በድጋሚ ከእነርሱ ጋር ኮሪያ ሆስፒታል ሄድኩ መርማሪ ፖሊስም የእርሷን ቃል ተቀብሎ አይኗን በምንድን ነው የወጋኸው አለኝ እኔም እስከ እዛ ጊዜ ድረሥ ምኗን እንደተጐዳች ሳላውቅ የምን ዓይን ነው የምትለው የምታወራው አልኩ አይኗም የተጐዳ መሆኑንም ያወኩት በዚያ ጊዜ ነው አንባቢ እንዲያውቅልኝ የምፈልገው ኤቢን ለመጉዳትም ሆነ እርሷ ላይ ችግር አደርሳለሁ ብዬ አንድ ቀን አሥቤበት አላውቅም ከእርሷ ጋር በተለያየ ጊዜ ሥሜቴንና ውስጤን በሚጐዳና በሚፈታተን ወቅት በተለይ በፍቺ ወቅት እንኳን እንደዛ ተጐድቼ እርሷን ለመጉዳት አንድም ቀን አስቤ አላውቅም፡፡ አብሬያትም ለ10 ዓመት በላይ ሥኖር እርሷ ተጐድታ እንዳታዝንብኝ እርሷን በጥንቃቄ ይዤ መኖሬ እንዲሁም እኔ ይህንን ድርጊት ፈፅሜ ቢሆን ከዚህ ልሰወርበት የምችል የተለያየ ነገር እያለኝ በተፈጠረው ሁኔታ አዝኜና እርሷ እንድትድንልኝ የማደርገው ጥረት ለእርሷ አሁንም ያለኝ ፍቅርና መውደድ ነው፡፡ ኤቢ አሁንም የማዝነውና የማስበው ወደ እስር/ጭለማ ህይወት መግባቴ አይደለም የእኔ ህይወት አጭር እና ምን አልባትም እንጥፍጣፊዋ የቀረች ቢሆንም የእኔ አይን ከእኔ ተወሥዶ ለአንቺ መብራት ቢሆንሽ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብና በእግዚአብሔር ፊት ቃል እገባልሻለሁ፡፡በሥተመጨረሻም የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ሴት እህቶቼና እናቶቼ በዚህ ድንገተኛ ያልታሠበ ክሥተት በእናንተ ዘንድ መጥፎ ሥዕል እንዲፈጠር ምክንያት በመሆኑ ባዝንም እኔም የምወዳቸው እህት እናት ያለኝና እንደዚህ ዓይነት ድርጊት የምፀየፍና የማወግዝ ሲሆን በተፈጠረው ሁኔታ መፀፀቴንና ማዘኔን በመግለፅ በእናንተ እና በፍትህ አካል ሊደርሥብኝ የሚችለውን ቅጣት ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡

 

 

 

Read 6567 times Last modified on Saturday, 31 December 2011 09:29