ሲንቄ ባንከ አ.ማ ከተለያዩ ስምንት ተቋማት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተፈራርሟል፡፡ ባንኩ ከተቋማቱ ጋር ከተፈራረማቸው የመግባቢያ ሰነዶች በተጨማሪ የ50 ሚሊዮን ብር የኢንቨስትመንት ስምምነት ከኢትዮጵያ የነዋይ ዋስትና ሰነዶች ልውውጥ ጋር ተፈራርሟል፡፡ ከባንኩ ጋር የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙት ተቋማት፣ ጨፌ ኦሮሚያ፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢኒስቲትዩት፣ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ፣ የኦሮሚያ ኢንደስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ፣ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ እና የኦሮሚያ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ናቸው፡፡