Saturday, 13 August 2011 09:15

ዘረክራካ ክህደት

Written by  ዶ/ር ፍቃዱ አየለfeke40ayema@gmail.com
Rate this item
(1 Vote)

ሐምሌ 30 ቀን 2003 ዓ.ም. በወጣችው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ..ግጥም..ያጠላባት ዘረክራካ ክህደት በመንማና መረጃ ተቆለማምጣ ተጥፋ አግኝቻት በትዝብት ጥሞና አነበብኳት፡፡ ይህች መጣጥፍ የዝርክርክ ክህደት ግዴለሽነትን ፍንትው አድርጋ መፈንጠቋ ብቻ ሳይሆን ሃይማኖት በፖለቲካ መተካቱ ካሰጋውና ታሪክ ከጠፋበት አላማኝ መመንጨቷም ግልጥ ነው፡፡ የመጣጥፏ ባለቤት በስንኞች ድርድራት ሳይሆን ነገራቸውን ያለ ልማዳቸው በዝርው በታትነው በነጻ አስተያየት መልክ ማመንጨታቸው ከሰበብነት የዘለለ ለዛ አልተገኘበትም፡፡ የግጥሙ ሰፈር ጭርታ ካላሳሰባቸው እና በዝርው መንዘርዘሩ ወዳላሰቡት ካምፕ አድርሶ ካላስደመማቸው ለሰበብነት መብቃትስ ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ለእኛ ለምናምን ደግሞ ያመንቷነውን እንተርከው ዘንድ ሰበብ ያላሳጣንን ለማመስገን ሌላ ሰበብ ሆኖልናል፡፡

ታዲያ ያች መጣጥፍ እምነተ ቢስነት ላይ የተወረወረው የእምነት ብእር ሹለትና ስለት እስከ ክህደት ኪነት ድረስ መዝለቋን ለማመላከት እንዳገለገለች በመቁጠር ለዚያ ሲባል ብቻ መጣጥፊቱን በእምነትና በታሪክ ሚዛን ላይ አውጥቼ ቀሊልነቷን ለማሳየት ወሰንኩ፡፡ ምንም እንኳ ያቺ መጣጥፍ ከፍተኛ ዝርክርክነትና የቅጥፈት ባዘቶ ያየለባት ብትሆንም ቅሉ አቅጣጫዋ ምላሽን የሚጋብዝ ሆኖ ስለታየኝ ..እምነታዊ ቀስቴን.. እነሆ ዛሬም በአዲስ አድማስ ወነጨፍኩኝ፡፡
በዚያች በሐምሌ 30ዋ መጣጥፍ ውስጥ ..እግዜር ያልተረጋገጠ መላምት ነው፤ ቅዱሳን መጽሐፍትም ዘመናቸውን እንጂ ዘመናችንን በማያውቁ ሰዎች የተጻፉ ድርሰቶች ናቸው ብሎ የሚያስብን ትውልድ ልቡን የሚመጥን መልስ እንጂ መቆጣት የሚያዋጣ አይመስለኝም.. የምትለዋ እምነት አልባዊ ማሳረጊያ ትውልድን የመወከል ከፍተኛ መንጠራራትን አይቼባት ተደንቄአለሁኝ፡፡ ምልልሱ ..የትውልድ.. ቁርቁስ አይደለም ..የእምነት እና የእምነተ ቢስነት.. እንጂ፣ ስለዚህ ትውልድን በደፈናው ሳይሆን አላማኙን ..ትውልድ.. ወክያለሁ ቢባል የሚሻል ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን በእምነት መንፈስ ለባነኑ አማኞች ክህደት የመንፈስ አሠራር ስለሆነ በእድሜና በፆታ አለመገደቡ በእምነት የተገለጠ ምስጢር እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ምስጢሩም የክህደት ክህደትን ከእምነት በፊት ሊታወቅ አለመቻሉ ነው፡፡ የካደ የተካደውን ህላዌ የሚለይ ..የውስጥ ሰውነቱ.. ተኮላሽቷልና የሚካድ መኖሩን ለመገንዘብ ብቃት ያጥረዋል ምክንያቱም ..የማያምኑትን ሃሳብ የዚህ ዓለም ገዢ አሳወረ.. ተብሎ ተጽፏልና፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ |እግዚአብሔር መላ ምት ነው.. መባሉን ተቀብዬ አላማኙን ከያኒ ደስ ላሰኛቸው እሻለሁ፡፡ በውልደቱና በሞቱ የተከረቸመ መስሎ ለሚሰማው እምነተ ቢስ እግዚአብሔርN በመላ ምት ደረጃ ለማውረድ የመሞከር ድፍረት አይከለከልም፤ ለምን ቢባል ሊፈራ የሚገባውን ፈጣሪን መዳፈር ለእርሱ የህይወት ትርጉም ሆኖለታልና፣ ምናልባትም የንብረቱ ምንጭ፡፡ ነገር ግን |እግዚአብሔር´ የተባለው መላ ምት ባለመረጋገጡ ጉዳይ ላይ አላማኙን ገጣሚ ጋር መለያየታችን ሳይታለም ተፈትቷል፡፡ እምነተቢሱ ገጣሚ |እግዚአብሔር´ የተባለውን መላ ምት እንዳልተረጋገጠ የሚያሳይ አንዲት ተጨባጭ መረጃ እንኳ መምዘዝ አለመቻላቸው በድጥ ላይ የመቆማቸው ማሳያ ነው፡፡ ምናልባት ከዚህ ቀደም ጠብ ገጥመዋቸው የነበሩትን ..የማያምኑ ሃይማኖተኞች.. በልብ ጥልቀት ውስጥ በማስረጃነት ሰውሮ እግዚአብሔር እንደሌለ ራስንና መሰል እምነተ ቢሶችን መደለል ይቻል ይሆናል፡፡ ነገር ግን |እግዚአብሔር´ የሚለውን ..መላ ምት.. በእንደዚያ ዓይነት ልኩስኩስ ክስተቶች ውድቅ ማድረግ ለሰበብነት እጅግ አናሳ ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔርN በግጥም ቅንጭብጫቢ ተሳድበው ሲያበቁ ..ቁጣው አልወደቀብኝምና አለመኖሩን አረጋግጫለሁ.. የሚል ..ገጣሚያዊ.. አዝማሚያ፣ ..አምነነዋል.. በነገራችን ላይ መላ ምት በግጥም ሊናም ሊሻርም አይችልም፤ በተጨበጠ መረጃ እንጂ፡፡ (ያልተረጋገጠ መላ ምት ነው) ብሎ መገገም ..በሲሉ ሰምታ.. ሊያስፈርጅ ይችላል እንጂ የመካጃ ካባ አድርገው ቢደርቡት ብዙም ሙቀት ሰጭ አይሆንም፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ..ክህደተ ምእምናንን.. ሊያጽናና የሚችል ..እግዜር የተባለው መላ ምት.. እንዴት እንደፎረሸ የሚያሳይ ሽራፊ ማስረጃ መወርወር አለመቻል የዝርክርክነት ልኬትና ውጤት ነው፡፡ ስለሆነም አንድን መላ ምት ውድቅ ለማድረግ ..ገጣሚነት.. ወይም ..ሌላ ነገርነት.. ብቻውን በቂ አይደለም፤ ምክንያቶችን መደርደር ግን በእንዲህ ዓይነቱ ተኩስ ውስጥ ምርጫ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነው፡፡ ይህ በግጥም ተደብቆ ማምለጥ የማይሞከርበት ፍልሚያ መሆኑን ተገንዝቦ አንዳንዶቹ እያደረጉ እንዳሉት መረጃዎችን ከምንጫቸው መቅዳት ለክህደትም ቢሆን በነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ለመንፈራገጥ ጠቃሚ ነው እንጂ ግጥምን እያውለበለቡ የክህደትን ከንቱነት ቁም ነገር ለማድረግ መታከር ነፋስን መጨበጥ ነው፡፡
..ፈሪሀ እግዚአብሔር ወይስ ዴሞክራሲ?.. ተብሎ ለተሰነዘረው መጠይቃዊ ርዕስ የርዕሱና የጽሑፉ ባለቤት፣ ..ዲሞክራሲ.. ብለው ለዲሞክራሲ ከፈሪሀ እግዚአብሔር ይልቅ ማጐብደዳቸውን ..መራራውን ሀቅ ለመጋፈጥ የሚፈልግ ሰው ካለ ዳቦና ዴሞክራሲ ከእምነት ኃይሎች እንደማይፈልቁ ማወቅ አለበት.. ከሚለው ድምዳሜያቸው ለመረዳት አይቸግርም፡፡ በእርሳቸው እይታ ዳቦ በዳቦ ለመሆንና በዴሞክራሲ ለመንበሽበሽ እግዚአብሔርN መፍራት ሳይሆን እግዚአብሔርN በደንብ አድርጐ መዳፈር አዋጭ ነው፡፡ እምነትም የዴሞክራሲ መርዝ ነው ብለው ያስባሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት ድምዳሜ በእምነትና እምነተ ቢስነት የተነሳውን የአዲስ አድማስ የጽሑፍ ምልልስ አቅጣጫ አጠማዞ ..ፖለቲካዊ ጭፈራ.. ለማስጨፈር የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ ሆኖም በታላቁ መጽሐፍ ላይ የተመሠረተ እምነት ሰውን ከየትኛውም አስተሳሰቡ ጭምር የማክበርና ለሰዎች እውነተኛ ነጻነት መጋደልን ያስተማረ ትክክለኛ የፖለቲካም ምንጭ እንደነበር ታሪክ በታላቅ ጩኸት የሚያውጀው ሀቅ ነው፡፡
በነገራችን ላይ በክህደታዊ ድፍረት የዮሐንስ ወንጌልን እንዳላነበበ ተደርጐ የተሳለው ቤንጃሚን ፍራንክሊን፤ የአሜሪካን ህገ መንግሥት በማርቀቁ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ የተናገረውን ብቻ መጥቀስ ክህደት የማይታየውን እግዚአብሔርN ብቻ ሳይሆን ሲያስፈልግ ደግሞ የሚነበበውን ታሪክም ቢሆን ለመካድ እፍረት ያጣ ብቃት ሊያመነጭ እንደሚችል ማመሳከሪያ ይሆነናል፡፡ ቤንጃሚን ያለውን አብረን እናምብበውማ “Gentlemen, if it is true that not one single petal from any flower falls to the ground without escaping God’s attention, will the distress of this nation go unheeded? Let us therefore determine to seek His face.” yእግዚአብሔርN ፊት በመፈለግ የተጉ ሰዎች ዛሬ መደነቂያ ብቻ ሳይሆን ለሌላው ዓለም ህዝብ እንደ ህልም የሚታሰብን ህገ መንግሥት ጽፈው ቢያልፉ ምክንያቱ ፊቱን ፈልገው ያላሳፈራቸው እግዚአብሔር ያስጨበጣቸው ጥበብ ነው፡፡ እምነተ ቢሱ ከያኒ ከአሜሪካን አባቶች ዋና ስለነበረው ፍራንክሊን የወሸከቱት ውሽከታ አንባቢን ምንም የታሪክ እውቀት የሌለው አድርጐ የማሳነስ ክፉ ባህሪ ስለሆነ ብዙ ባያስደነቅም ሊታረም ግን ይገባዋል፡፡
ቤንጃሚን ፍራንክሊን አማኝ ሆኖ መገኘቱ ልክ ሌሎች አማኝ የነበሩ ደግሞም እግረ መንገዳቸውን ይህ ዓለም የሚያሸረግድለትን የእውቀት ዓይነት እምነተ ቢሶች ሊገምቱት ከሚችሉት በላይ ታጥቀው መገኘታቸው ሲያስበረግጋቸው እንደኖረ የፍራንክሊንም ነገር በዚሁ መልክ የሚታይ ነው፡፡ አንድ ሁሉ የሚስማማበት ሀቅ ግን አለ፤ እሱም ቤንጃሚን ፍራንክሊን እጅግ የሚያምን መሆኑና ታላቁ መጽሐፍ የታላቅነት ምንጭ መሆኑን መገንዘቡ ነው፡፡ በ1787 ዓ.ም. ቤንጃሚን ፍራንክሊን ከተናገረው አንዲት ማጣቀሻ ብቻ ልምዘዝና የሐምሌ 30ውን ዘረክራካ ክህደት ምንነት በታሪክ አብነት ላራቁተው “I lived a long life and the longer I live the more convincing proofs I see of this truth that God governs in the affairs of men.” ወደ አማርኛ ስንቀለብሰው ..ረዥም ዘመን ኖሬያለሁኝ እድሜዬ በጨመረ ልክ ስለዚህ እውነት አሳማኝ የሆኑ ማረጋገጫዎችን ተመልክቻለሁኝ፡፡ ይህም እግዚአብሔር የሰዎችን ጉዳይ መምራቱ ነው፡፡.. ይህ አባባል የክህደትን ባንዲራ ቦጫጭቆ ለቅርጫት የዳረገ በመሆኑ ከተስማማን ተናጋሪው ቢያንስ ቢያንስ በክህደት እስር ቤት አለመከርቸሙ ግልጽ ይሆንልናል፡፡ ይህ ሰው የአሜሪካንን አብዮት ለአሜሪካኖች ጥቅም ካዋሉት መሥራቾች አንድ ምሳሌ ብቻ የሆነው ፍራንክሊን ነው፡፡
በነገራችን ላይ የእኛ ሀገር አላማኞች በእምነታቸው ንተው ቆመው ለብዙ ሰዎች ነጻነት ምክንያት የሆኑ ባለታሪኮችን ወደ ክህደት እንጦረጦስ ጎትተው ለመድፈቅ የሚወራጩት በክህደት ብርቱ የነበሩ ሰዎች ጠፍተው አይደለም፡፡ በአደባባይ ክህደትን መስበክ ብቻ ሳይሆን መካድና እምነተ ቢስነት ..በሳይንስ.. መልክ እንዲቆነን ያደረጉ አብዮተኞች ሞልተውላቸዋል፣ ግን ሳይንሳዊ ክህደታቸው በታሪክ የተብጠለጠለ ብቻ ሳይሆን የህዝብን ደም እንደጎርፍ ያጎረፈ ታሪክ ብቻ ያላቸው ስለሆኑ ለአደባባይ ማጣቀሻነት አይገለገሉባቸውም፡፡ ፈጣሪን በአደባባይ የካዱ ሰዎች እነ ማርክስ፣ ኤንግልስ፣ ሌኒን፣ ሞሰሎኒ፣ ሂትለር፣ ማኦ እና ሌሎችም ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ጉልበት ባገኙ ጊዜ ሰው ሁሉ ሊታረድ የሚገባው የፋሲካ ዶሮ መስሎ ይታያቸው እንደነበር ታሪክ የጠፋቸውን እኝህን ከያኔ ማስታወስ መልካም ይመስለኛል፡፡ ሞት ክህደትን ለብሶ ታሪክን ሲተርክ መገልገያ ሆነው ራሳቸውን ያቀረቡት እነዚህ ከሃዲያን ነበሩ፡፡ እናም ለክህደት ምሳሌ መጥቀስ ካስፈለገ ከእምነት ሰፈር እምነትን በዜሮ እያባዙ ሳይሆን ከዛው ከክህደት ሰፈር ማማረጡ ቢያሳፍርም የሚሻል ይመስለኛል፡፡ ግልጽ መሰለኝ፡፡
የሐምሌ 30 እምነተ ቢስ ገጣሚ ታዲያ ..ሃይማኖት ርዕሰ ጉዳይ.. የተደረገ ለማስመሰል እምነትና እምነተ ቢስነት ከየጎራቸው የሚለዋወጡትን የሃሳብ ተኩስ ሃይማኖታዊ አድርገው በተለመደ የእምነት አልባውያን ሃኬት መንፈሳዊነትን ከሃይማኖት ጋር የማመሳሰል መላን ለመጠቀም ከጅለዋል፡፡ ሃይማኖት አይደለም ርዕሰ ጉዳዩ ..እምነት እና እምነተ ቢስነት.. እንጂ፡፡ ከዚህ ቀደም በተጻፉት ጽሑፎች እምነት አልባውያን እምነትን የማጣጣል ዘመቻቸውን ከፍልስፍናና ከሳይንስ ጋር አቆራኝተው ..ፍልስፍናና ሳይንስ ርስታችን.. ነው የሚሉት ቅንጡነትን ማስፋፋታቸው ነው ብዕራችንን በእምነተ ቢስነት ላይ ያስወደረን፡፡ አለማዊ በተባሉ ጋዜጦች ላይ ለብዙ ዘመናት ያለማንም ተቀናቃኝ ..እምነትን.. በዶለደመ የብዕር ጦር ያወደሙ እየመሰላቸው ለከረሙት የክህደት ቀሳውስት፤ እምነት በክህደት ሊዳፈን የማይችል መሆኑን ለማሳየት ነው እየጻፍን ብቅ ያልነው፡፡ አለማመን በቂ መሠረት የሌለው ለመሆኑ ፍልስፍናንም ሳይንስንም እየጠቃቀሰን አሳይተናል፤ ምናልባትም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ ይህን እንቀጥላለን ምክንያቱም ያመንነውን እናውቃለንና፡፡
እምነተ ቢሱ ከያኒ ታዲያ ፖለቲካንም ከእምነት ለመዘንጠል እና ፖለቲካቸውን በታላቁ መጽሐፍ ትምህርት መመሥረታቸውን ታሪክ የመሰከረላቸውን ሀገሮች ከእምነት በመነጠል ከፍተኛ መጣጥፋዊ ክህደት እና ቅጥፈት ፈጽመዋል፡፡ ሐፊው በአሜሪካ ጉዳይ ላይ በትልቁ ለመዋሸታቸው ምስክር የምጠራው ከአሜሪካ ፕሬዝደንቶች አንዱ የነበሩትን አንድሪው ጃክሰንን ነው “That book, sir, is the rock on which our republic rests” ሲሉ የተናገሩት ታላቁን መጽሐፍ ለማጣጣል ለሞከረ አንድ ከሃዲ ሰው ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እጅግ ብዙ ማለት ቢቻልም በተለይ የአሜሪካ አማኝ ፖለቲከኞች ራሳቸው ስለ ሀገራቸው ያሉትን በጥቂቱ መጠቃቀስ በቂ ይመስለኛል፡፡ የፈረንጅ ስም ሲጠራ ፊታቸው የሚፈካ እምነት አልባውያን የአሜሪካ ስኬት የተቀዳው ከታላቁ መጽሐፍ አለመሆኑን በወልጫማ ብእር ክደው ለማስካድ ቢዳክሩም ቀንደኛው አማኝ ፕሬዝደንት አብርሃም ሊንከን ስለ ታላቁ መሃፍ ያለውን ላስነብባችሁ “I am profitably engaged in reading the Bible. Take all of this book upon reason... balance by faith, and you will live and die a better man.” እምነት ከዚህ በላይ እንዴት ሊገለ ይችላል? አብርሃም ሊንከን ግን ከዚህም በላይ ይችልበታል፡፡ ይኸው ያለውን ደግመን እናምብብ “I believe the Bible is the best gift God has ever given man. All the good from the Savior of the world is communicated to us through this book. Except for it we could not know right from wrong” እንደዚህ የሚያምኑትን የአሜሪካ መስራች አባቶች ነው የሃምሌ ሰላሳው አላማኝ ከያኔ ለአሜሪካ ..የፖለቲካ ስርአቷን መስራች አባቶቿ በዘመነ መባነን (xþNላይTmNT) አስተሳሰብ እንጂ በመሃፍ ቅዱስ የሚመሩ አልነበሩም.. ሲሉ ስተው ለማሳሳት የሚፉት፡፡ ጆርጅ ዋሽንግተን ግን አለምንና ሃገሩን ስለመምራት ሲናገር “it is impossible to rightly govern the world without God and the Bible” ነው ያለው፡፡ ይህ አባባል ከሶስት መቶ አመታት በፊት አማኝ የሆነ መሪ የተናገረው ትንቢታዊ ቃል ነው፡፡ ይኸው ጆርጅ ታዲያ  “Do not let anyone claim tribute of American patriotism if they even attempt to remove religion from politics” ብሎ ከሃዲያን ሳይናገሩና ሳይፉ በፊት የአሜሪካንን ታላቅነት ምክንያት ሊስተባበል በማይችል መልኩ አጠቃሎታል “God and the Bible” ብሎ ሮናልድ ሬገን ስለ ታላቁና አስገራሚው መጽሐፍ  “indeed, it is indisputable fact that all the complex and horrendous questions confronting us at home and world wide have their answer in that single Book” ማለታቸው የምርጫ ውድድር ለማሸነፍ ሲሉ እንጂ ሃገራቸው ከዛ መጽሐፍ ስትኮመኩም የኖረችውን ጥቅም አስበው አይደለም ካልተባለ በቀር ሰውዬው አማኝ ለመሆናቸው አንድ ትንሽዬ ምሳሌ ነች፡፡
ህሊናን በትርኪ ምርኪ እውቀት ቀብሮ ሃጢአትን እንደ ኮሶ መጋት ነፃነት የሚመስላቸው እምነተ ቢስ ሰዎች፤ እግዚአብሄርን መፍራት ባርነት ቢመስላቸው ብዙም አስደናቂ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ መሃፉንም ይህንን አስተሳሰባቸውን የደገፈ በመሰላቸው ጊዜ ቢጠቅሱት ትክክል ናቸው፡፡ ታዲያ የሃምሌ ሰላሳውም እምነት አልባ ገጣሚ ..ለጌታ ብላችሁ ለሰው ስርዓት ተገዙ.. የሚለውን ትእዛዝ ..ለጥ ሰጥ ብላችሁ ተገዙ.. ብሎ ቃሉ እንዳስተማረ አድርገው አጣመው ጠቅሰዋል፡፡ እነዚህና የታላቁ መጽሐፍ መሰል ሃይለ ቃሎች ሰው ..ግፍን ጭው አድርጐ እንዲጠጣ.. ባርነትን የሚሰብኩ አይደሉም፡፡ ይልቁንስ ለሃገር ደንብና ስርዓት የምትታዘዙት ህጉን ያወጣውን ሰውዬ/ሴትዮ ብላችሁ ሳይሆን እግዚአብሄርን ብላችሁ ሊሆን ይገባል ነው፣ ምክንያቱም እነዚህ ክፉውን ለመቅጣት በጐውን ለመሸለም ..ከእርሱ ተልከዋልና.. ብሎ ነው የሚያስተምረው፡፡ ከእርሱ ያልተላኩ በሆኑ ጊዜስ? ማለትም በጐ የሆነውን ሰው እየቀጡ፣ ክፉ የሆነውን ሰው በአደባባይ የሚያመሰግኑና የሚሸልሙ ሲሆኑስ? ለእንደዚህ አይነቶች ተገዙ አይልም፡፡ ለዚህ ማስረጃ ባህር መሻገር የሚገባ አይመስለኝም፡፡ በእምነት አልባውያን በእምነቱ ምክንያት የሚብጠለጠለው የዚህ ሀገር ህዝብ፤ ብዙ ጊዜ በገዢዎቹ ላይ ያመፀው ክህደትን ለማስፋፋት ወይንም እምነተ ቢሶችን ለማስጨብጨብ ፈሞ አይደለም፡፡ የግፈኞች ዋ ሲሞላ እግዚአብሄር በግፈኞች ላይ ይነሱ ዘንድ የሰዎችን ልብ ለአመ ማነሳሳቱ አይቀርም፡፡ ስለዚህ ነው ንጉስም ይሁን፣ መኳንንትም ይሁን በደልን ወደ ግፍ ዋ ማንደቅደቅ ሲጀምር የፍፃሜው መጀመሪያ የሚሆነው፡፡ ትክክለኛ ፈራጅ እግዚአብሄር ነው፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡ እንግዲህ ማሳረጊያዬን የሃምሌ ሰላሳዋን ዘረክራካ ክህደት ለማድቀቅ ከታላቁ መሪ አብርሃም ሊንከን በወሰድኳት አባባል ላጠናቅቅ “My concern in not whether God is on our side. My Great concern is to be on God’s side, for God is always right.” እንዲህ አይነት መሪ እግዚአብሄር ይስጠን፡፡

 

Read 3145 times Last modified on Saturday, 13 August 2011 12:47