Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 27 October 2012 11:12

“ኩራት በሃገር ልብስ” ዛሬ ይቀርባል

Written by 
Rate this item
(3 votes)

ሚራክል ዲዛይን ፋሽን ተቋም ለሰባት ወራት ያሰለጠናቸው 102 ተማሪዎች ያዘጋጁዋቸው ልብሶች የሚታዩበት “ኩራት በሃገር ልብስ” የፋሽን ትርኢት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ ገለፁ፡፡ 92 ሴቶች እና 10 ወንዶች በሚሳተፉበት ትርኢት በሚደረገው ውድድር አንደኛ የሚወጣ (የምትወጣ) በሕንድ ሀገር የስድስት ወራት ተጨማሪ ትምሕርት እንደሚመቻች አዘጋጆቹ ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል፡፡

በፕሮፌሽናል ሞዴሎች የሚቀርበውን ትርኢት አስመልክቶ የተቋሙ ባለቤት እና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት መላኩ ለዝግጅት ክፍላችን ሲገልፁ፤ በአለባበስ ላይ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሠሩና የሐገር ባህል ልብሶች እንደሚያበረታቱ ጠቁመው፤ ከጠሯቸው 700 እንግዶች አብዛኞቹ ልብስ ዲዛይነሮች፣ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ሐላፊዎችና አርቲስቶች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
በውድድሩ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ለሚወጡም ነፃ የሐገር ውስጥ አጭር ተጨማሪ ሥልጠና መዘጋጀቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Read 3127 times

Latest from