በፕሮፌሽናል ሞዴሎች የሚቀርበውን ትርኢት አስመልክቶ የተቋሙ ባለቤት እና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት መላኩ ለዝግጅት ክፍላችን ሲገልፁ፤ በአለባበስ ላይ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሠሩና የሐገር ባህል ልብሶች እንደሚያበረታቱ ጠቁመው፤ ከጠሯቸው 700 እንግዶች አብዛኞቹ ልብስ ዲዛይነሮች፣ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ሐላፊዎችና አርቲስቶች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
በውድድሩ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ለሚወጡም ነፃ የሐገር ውስጥ አጭር ተጨማሪ ሥልጠና መዘጋጀቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡