Print this page
Saturday, 04 February 2023 18:45

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሦስት ቀናት የሃዘን፣ የፆምና ጸሎት ጊዜ አወጀች

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(35 votes)

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ለ3 ቀናት ጥቁር እንዲለብሱም አዝዛለች
               
        የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የፊታችን ሰኞ በሚጀመረው ፆመ ነነዌ፣ ሁሉም የእምነቱ ተከታዮች ጥቁር ልብስ በመልበስ፣ በጾምና ጸሎት በመትጋት ፈጣሪውን እንዲማጸን ጥሪ አቅርባለች።
ቅዱስ ሲኖዶስ ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ ቤተክርስቲያኒቱ በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ ከፍተኛ ሃዘን ላይ መውደቋ ተገልጿል። በዚህም የፊታችን ሰኞ በሚጀመረው የ3 ቀናት የነነዌ ፆም፣ ጥቁር ልብስ በመልበስና ክርስቲያን በመከራ የሚፀና መሆኑን በመግለጽ፣ ወደ እግዚአብሔር ጾም ፀሎትና ምህላውን እንዲያሰማ ጥሪ ተደርጓል።
“ጥቁር የእውነት ምልክት ነው። ዳኞች እውነትን እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ይለብሳሉ” ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ፤ “እኛም መከራው የሚያሳቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባን መሆኑን ለዓለም ህዝብ የምናሳይበት ነው” ብሏል። ከጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ለ3 ቀናት በሚቆየው በዚሁ የነነዌ ጾም፣ በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ጥቁር ልብስ በመልበስ፣ በአንድ ልብ ሆነው ፈጣሪቸውን በፆምና በፀሎት እንዲማጸኑ ጥሪዋን አስተላልፋለች።

Read 2791 times