Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 27 October 2012 10:50

ግሪክ ኮሙኒቲ ተማሪዎች የመንግስታት ድርጅት ቀንን አከበሩ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ከሃምሳ በላይ ሀገራት የተውጣጡ የግሪክ ኮሙኒቲ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀንን በትምህርት ቤታቸው ቅጥር ግቢ ከትናን ወዲያ ረፋድ ላይ በተለያዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶችና የየሀገራቱን ባንዲራ ይዘው በመሠለፍ አከበሩ፡፡
“የሕፃናት ጋብቻ ይቁም” በሚል መርህ በተከበረው በዓል ላይ ተማሪዎች የተለያዩ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን አንድነት የሚያሳዩ የብሔረሰቦች ዘፈኖችን፣ የግሪክ የምዕራብ አፍሪካ እና የአረብ እንዲሁም የብሬክ እና ትዊስት ዳንሶችን ለክብር እንግዳው አዲሱ በኢትዮጵያ የግሪክ አምባሳደር እና ሌሎች እንግዶች አሳይተዋል፡፡

የትምህርት ቤቱ መምህርና የዝግጅቱ አስተባባሪ ዮሴፍ ፍራንሲስ ይህንኑ አስመልክቶ ለአዲስ አድማስ ሲናገሩ አንድ ሺህ ተማሪዎች ያሉት ትምህርት ቤታቸው የመንግስታቱን ድርጅት ቀን ላለፉት 15 ዓመታት ሲያከብር መቆየቱንና ተማሪዎቹ ዘር፣ ቀለም ዜግነት ሳይለዩ አብሮነትን እንዲያዳብሩ አግዟል ብለዋል፡፡
ከክብር እንግዶች አንዷ የሆኑት የተባበሩት መንግስታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ተጠሪ የእርስ በርስ ያህል መከባበርን ወሰን ሙላቱ ሕብረ ባህል ያላቸው ተማሪዎች እንዲህ ማክበራቸው አብሮ መኖርንና ትእግስትን እንዲያጣምሩ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡ በትምህርት ቤቱ የእስራኤልና ፍልስጤምን ጨምሮ ከተለያዩ ሃምሳ ሀገራት የተውጣጡ ተማሪዎች ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ይማራሉ፡፡
በትምህርት ቤቱ ልጃቸውን የሚያስተምሩትና በግል የተጋበዙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ምህረት ደበበ በዓሉን ከታደሙ በኋላ “በዓሉ ተማሪዎቹን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ ስለመንግስታቱ ድርጅት በማወቅ ሰላም ወዳድ ዜግነታቸውን ያዳብሩበታል” ሲሉ አስተያየት ሰጥተውናል፡፡

Read 2254 times