“ያውዌ” የተሰኘ መጠሪያ ያለው የሙዚቃ ኮንሰርት ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ጊዮን ሆቴል ውስጥ በሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ዎክ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ በእለቱም በጉራጊኛ ድምፃዊነታቸው ተወዳጅነትን ያተረፉት ድምፃዊያን ሀና ተሰማ(ያውዌ) ፣ ደምሴ ተካ፣ ፀጋዬ ስሜ (ሆሴ ባሳ)፣ ሀይሉ ፈረጃ ፣ ደሳለኝ መርሻ፣ ፈለቀ ማሩ ፣ አምደ ገብርኤል አድማሱ ፣ ግዛቸው ተሸመና የባህል ድምፃዊው ደመረ ለገሰ ፣ ስዩም ጥላሁን (አንቺ ወረተኛ)እና ሌሎችም ተወዳጅ ድምፃዊያን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
የመግቢያ ዋጋው መደበኛው 500 ብር ቪአይፒው 1000 ብር ሲሆን ሁሉም በቴሌ ብር በኩል እንደሚገኙ የኮንሰርቱ አዘጋጅ “መደሰቻ” መልቲ ሚዲያ አስታውቋል፡፡