Saturday, 28 January 2023 21:18

“ጥቁር አዳኝ”

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(5 votes)

ትርጉም መፅሀፍ ለንባብ በቃ
 
  ከ30 ዓመት በፊት በሩዋንዳ በሁቱና ቱትሲ ጎሳዎች መካከል የተፈጠረውን የዘር ፍጅትና በ90 ቀናት ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ንፁሀን እንደቅጠል የረገፉበትን ታሪክ የሚያስቃኘው “An Ordinary Man”  የተሰኘ መፅሀፍ በትርጓሚ ታጠቅ ከበደ “ጥቁር አዳኝ” በሚል ወደ አማርኛ ተመልሶ ለንባብ በቃ፡፡
በዘር ፍጅቱ ወቅት በሩዋንዳ (ኪጋሊ) ውስጥ የአንድ ሆቴል ማናጀር የነበረው  ፖል ሩሴሳባጊና በእንግሊዝኛ የተፃፈው ሲሆጀን ፀሀፊው ግለ ታሪኩን፣ የወቅቱን አጠቃላይ የፍጅት ታሪክ፣ የራሱን የልጅነት ጊዜ ትዝታዎች ፣ የቤተሰቡን ህይወት ፣ የሩዋንዳን ታሪክና ባህል እንዲሁም ወደ ዘግናኙ የዘር ፍጅት ያመሩበትን ምክንያቶች ያካተተበት ድንቅ መፅሀፍ ነው ተብሏል፡፡
ፀሀፊው ፖል ከሁለቱ ቤተሰብ የተወለደ፣ ቱትሲ ሚስት ያገባና ከሁለቱ የተገኙ ቅይጥ ልጆች አባት ሲሆን በዚህ ምክንያት የደረሰበትንም ፍዳ በመፅሀፉ አካትቷል ተብሏል፡፡
ይህን መፅሀፍ ወደ አማርኛ መመለስ ያስፈለገበትን ምክንያት ተርጓሚው ሲገልፁ ለዚህ ዘግናኝ የዘር ፍጅት ሚዲያዎች፣ የሀይማኖት ተቋማትና መሪዎች የነበራቸው ተሳትፎ ያስከተለውን የማይድን ቁርሾ ያልተገቡ ትርክቶችና አረዳዶች የሚያመጡትን ጦስ ለሀገራችን ህዝብ በማሳየት ከዚህ ትምህርት ወስደን ያሉብንን ችግሮች ለመፍታት ይረዳን ዘንድ ነው ተብሏል፡፡ መፅሀፉ በ264 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ11 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን በ300 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል፡፡

Read 3624 times