Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 27 October 2012 10:47

“ከለርስ ኦፍ ዘ ናይል” ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

“ከለር ኦፍ ዘ ናይል” ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ከጥቅምት 28 እስከ ህዳር 2 ቀን 2005 ዓ.ም በብሔራዊ ቲያትር ይካሄዳል፡፡ በፊልም ፌስቲቫሉ ከ28 ሀገሮች የተዉጣጡ 58 ምርጥ የአፍሪካ ፊልሞች ለዕይታ ይበቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ለዕይታ ከሚቀርቡት ፊልሞች መካከል የአልጀሪያ፤ የቡርኪናፋሶ፤ የካሜሮን፤ የኮንጎ፤ የግብፅ ፤ የኢትዮጵያ እና ሌሎችም በርካታ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ፊልሞች ይገኙበታል፡፡ በፊልም ፌስቲቫሉ ላይ በሶስት ዘርፎች በሚወዳደሩ የፊልም ስራዎች 10 ሽልማቶችን እንደሚሰጥ የገለፁት አዘጋጆቹ፤ ሶስቱ ዘርፎች በምርጥ ፊቸር ፊልም ፤ በዶክመንተሪ እና በአጭር ፊልም ዘርፍ የተከፈሉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ በምርጥ ፊቸር ፊልም ‹‹ዘ ግሬት ናይል አዋርድ›› ለተሰኘው ሽልማት ከሚወዳደሩ 8 አፍሪካዊ ፊልሞች መካከል “ሎሚ ሽታ” የተባለው ፊልም የቀረበውን መስፈርት አሟልቶ ኢትዮጵያን የሚወክል ብቸኛ ፊልም እንደሆነም ታውቋል፡፡ ውድድሩን የሚዳኙት ባለሙያዎች ከደቡብ አፍሪካ፣ ከጋና፣ ከፈረንሳይ፣ ከሆላንድ ከአሜሪካ እና ከኢትዮጵያ የተውጣጡ ናቸው፡፡

በፊልም ፌስቲቫሉ ሳምንት በተጓደኝ ልዩ ልዩ ስልጠናዎች፣ የፊልም ሂስ፣ የፊልም ድርሰት አፃፃፍ የድምፅ እና ፕሮዳሽን በሚሉ እና በሌሎችም ተያያዥ ዘርፎች ለኢትዮጵያውያን ፊልም ስራዎች ከልዩ ልዩ አገሮች በመጡ ባለሙያዎች ትምህርት ይሰጣል፡፡በተያያዘም በዚህ ፌስቲቫል ላይ ለመገኘት አርባ የፊልም ባለሞያዎች ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓ እና ከአሜሪካ እንደሚገቡ የታወቀ ሲሆን በፊልሙ አለም ከፍተኛ ተደማጭነት እና ተነባቢነት ያላቸው የመዝናኛ ኢንዱስትሪ የዜና አውታሮች የሚዲያ ሽፋን እየሰጡ ነው፡፡ እስከ አሁን Screen International, Film Contact, Indewire የተባሉትን ጨምሮ ከ 21 በላይ የፊልም መጽሔቶችና ጋዜጦች እንዲሁም ድረገጾች ፌስቲቫሉን አስመልክተው ልዩ ልዩ ዘገባዎችን አሰራጭተዋል፡፡“ከለርስ ኦፍ ዘ ናይል ፌስቲቫል”ን ያዘጋጀው ብሉ ናይል ፊልም እና ቴሌቪዥን አካዳሚ ከኢትዮጵያ ፊልም ስሪዎች ማህበር ጋር በመቀናጀት ሲሆን የአካዳሚው መስራች እና ስራ አስኪያጅ ሲኒማቶግፈር አብርሃም ሃይሌ ፌስቲቫሉን በፕሬዝዳንትነት በመምራት ላይ ይገኛል፡፡አብርሃም ሀይሌ ካሁን ቀደም “ዳራት” እና “አቡና” በተሰኙ ፊልሞች ከፌስፓኮ ፊልም ፌስቲቫል በምርጥ ሲኒማቶግራፍነት ሁለት ጊዜ ተሸላሚ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

Read 2413 times