Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 27 October 2012 10:44

“ግመ ፍቕሪ” ዛሬ በመቀሌ ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በተፈሪ ወልደኪዳን ተፅፎ አታክልቲ ነጋ (ጌይፀ) ያዘጋጀው የ105 ደቂቃ “ግመ ፍቕሪ” የትግርኛ ፊልም ዛሬ በመቀሌ ከተማ እንደሚመረቅ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ በከተማዋ በሚገኘው የሰማዕታት ሐውልት አዳራሽ ከቀኑ 8 ሰዓት በሚመረቀው የፍቅር ፊልም ላይ ጎይቶም ተወልደ፣ አዲያም ካህሳይ፣ ኢያሱ ገብረእግዚአብሔር እና ሌሎችም ይተውናሉ፡፡ ዛሬ በመቀሌ የሚመረቀው ፊልም በአዲግራት፣ በውቅሮ፣ በአክሱም፣ በአድዋ እና በሌሎችም የትግራይ ከተሞች የሚታይው ሲሆን የአማርኛ ትርጉም ከተሰራለት በኋላ በጎንደር እና በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎችም የሐገሪቱ ከተሞች እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

Read 1419 times