Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 27 October 2012 10:39

ሮድ ስትዋርት መፅሃፍ አሳተመ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ሮድ ስትዋርት በግል ህይወቱና ሙያው ላይ ያተኮረ መፅሃፍ ለንባብ አበቃ፡፡ “ሮድ ዘ አውቶባዮግራፊ” መፅሃፉ በአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነቱና በፍቅር ህይወቱ ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡ ከልጅነት እስከ እውቀት ያለፈበትን የህይወት ጎዳና በአዝናኝ አተራረክ እንዳቀረበው የ67 ዓመቱ ሙዚቀኛ ተናግሯል፡፡ ሮድ ስትዋርት “ሜሪ ክሪስማስ፡ ቤቢ አልበም” የተባለውን አዲስ አልበሙን በመጪው ሳምንት ለገበያ እንደሚያቀርብም ታውቋል፡፡

ሮደሪክ ዴቪድ ስትዋርት በሚል ሙሉ ስሙ የሚታወቀው እንግሊዛዊው ሙዚቀኛ፤ 115 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት እንዳለው ሰንደይ ታይምስ የሃብታሞችን ደረጃ ለማወቅ በሰራው ጥናት አረጋግጧል፡፡ ሮድ ስትዋርት በ50 ዓመት የሙያ ዘመኑ ከ200 ሚሊዮን በላይ የአልበሞቹን ቅጂዎች ሸጧል፡፡

 

Read 2019 times Last modified on Saturday, 27 October 2012 10:42

Latest from