በቦሊውድ ለረጅም ግዜ በዲያሬክተርነት ከሰሩ ምርጥ እና አንጋፋ ባለሙያዎች በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስም ነበር፡፡ ያሽ ቾፕራ በ80ዎቹ የሰራቸው የፍቅር ፊልሞች ዘመን የማይሽራቸው ምርጥ ስራዎች እንደሆኑ “ዘ ሂንዱ ታይምስ” ሲዘግብ፤ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የህንድ ሲኒማ ኢንዱስትሪ ታላቅ ባለሙያ ማጣቱን በሃዘን ገልፀዋል፡፡ ከያሽ ቾፕራ ጋር ከሰሩ ታዋቂ የቦሊውድ ተዋናዮች አሚታን ባቻ እና ሻሩክ ካህን ይጠቀሳሉ፡፡የሮማንቲክ ፊልሞች ንጉስ በሚል የሚወደሰው ያሽ ቾፕራ፤ ባለሃብቶችን ወደ ቦሊዉድ በመሳብ ትልቅ ሚና መጫወቱም ይነገርለታል፡፡ ባለፉት ሃምሣ ዓመታት በቦሊውድ ምርጥ ደረጃ ያላቸውን ከሃምሣ በላይ ፊልሞችንም ሰርቷል፡፡