Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 27 October 2012 10:34

የሃሎዊን ገበያ በሆሊውድ መሟሟቅ ጀመረ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ባለፈው ሳምንት ለእይታ የበቃው አስፈሪ ፊልም “ፓናሮማል አክቲቪቲ 4” የተሰኘው አስፈሪ ፊልም በሶስት ቀናት በሰሜን አሜሪካ ከሺ በላይ ሲኒማ ቤቶች ውስጥ ለእይታ በቅቶ 30.2 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት ቦክስ ኦፊስን እየመራ መሆኑን ሲኤንኤን አስታወቀ፡፡ “በፓርማውንት ፒክቸርስ በ5 ሚሊዮን ዶላር የተሰራው “ፓናሮማል አክቲቪቲ 4” የሆሊውድ ፊልሞችን የሃሎዊን ገበያ መልካም ጅማሮ አሳይቷል፡፡ የፊልሙ የመጀመርያ ሶስት ክፍል ፊልሞች በድምሩ 8ሚሊዮን ዶላር ወጪ ሆኖባቸው በመላው ዓለም 576.6 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቶባቸዋል፡፡ የመጀመርያው ፓራኖርማል ከሶስት ዓመት በፊት ለእይታ ሲበቃ 193.4 ሚሊዮን ዶላር፤ ሁለተኛው 177.5 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ሶስተኛው ባለፈው ዓመት 205.7 ሚሊዮን ዶላር አስገብተዋል፡፡

በአሜሪካውያን የሃሎዊን ክብር በዓል የዋዜማ ሰሞን የሆሊውድ ፊልም ሰሪዎች በአስፈሪ ፊልሞች ገበያቸውን እንደሚያሟሙቁ “ኢንተርቴይመንት ዊክሊ” ዘግቧል፡፡ በአሜሪካ ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጣቸው በዓላት በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የሃሎዊን ክብረ በዓል በፊልም ስራዎች እና በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች እስከ ስምንት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረግበታል፡፡

 

Read 2355 times Last modified on Saturday, 27 October 2012 10:39

Latest from