Saturday, 17 December 2022 13:00

የገና ባዛር የፊታችን አርብ በሚሊኒየም አዳራሽ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  “አስቤዛ” ባዛርም ጎንለጎን ይካሄዳል ተብሏል
                
        በንግድና ባዛር እንዲሁም በመዝናኛ ዝግጅቶች ቀዳሚ የሆነው ጆርካ ኢቨንትስ ያዘጋጀው የገና ባዛር የፊታችን አርብ ታህሳስ 14 ቀን 2015 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚከፈት አስታወቀ፡፡ እስከ ታህሳስ 28 ለ15 ቀናት በሚዘልቀው በዚሁ ባዛር ከ350 በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ትልቁ የገና ባዛር ላይ እንደሚሳተፉ ጆርካ ኢቨንትስ ትላንት ረፋድ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ በሰጠው ጋዜጠዊ መግለጫ አስታውቋል። አዘጋጁ ጆርካ አክሎ እንዳስታወቀው ከዚህ ቀደም የማህበረሰቡን ህይወት ጫና ውስጥ የከተተውን የኑሮ ውድነት ለማቃለል “አስቤዛ ባዛርን” ያዘጋጅ እንደነበር አስታውሶ በገና በዓል ህዝቡ ለበለጠ ጫና እንዳይጋለጥ በማሰብ ከገና ባዛር ጎንለጎን አስቤዛ ባዛር እንደሚካሄድ የጆርካ ኢቨንትስ ማርኬቲንግ ሀላፊ አቶ ሳምሶን ሀይለየሱስ አስታውቀዋል፡፡
ባዛሩ ለቀጣዮቹ 15 ቀናት በየቀኑ በተወዳጅ ድምፃውያንና በእውቅ ዲጄዎች የደመቀ ኮንሰርት የሚያቀርብ ሲሆን ማህበረሰቡ ለበዓሉ የሚሆኑ ግብአቶችንም ሆነ ለመደበኛ ኑሮው የሚጠቀምባቸውን ማንኛውንም አይነት እቃዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸመተ በኮንሰርቱ እየተዝናና በዓሉን መቀበል ይችላል ተብሏል፡፡
ሸማቹ ማህበረሰብ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ለገና ባዛር ሲመጣ ልጆቹን ይዞ በመምጣት ማዝናናት የሚችልበት ሙሉ ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን በቂ የመኪና ማቆሚያ ከአስተማማኝ ጥበቃ ጋር በማዘጋጀቱ ሁሉንም በአንድ ቦታ ማግኘት ይችላል ብለዋል አዘጋጆቹ።


Read 11638 times