Saturday, 12 November 2022 13:07

“እንዳትጋቡ” መፅሀፍ በድጋሜ ታትሞ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በደራሲ ዳይሬክተርና የትዳር አማካሪ ሱራፌል ኪዳኔ የተፃፈውና ጤናማ የትዳር ህይወትን ለመምራት የሚያስችሉ በርካታ ቁምነገሮችን የያዘው “እንዳትጋቡ” የተሰኘ መፅሀፍ በድጋሚ ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡
ደራሲና ዳይሬክተር ሱራፌል ባለፉት 16 ዓመታት በትዳር የቆየና የሶስት ልጆች አባት ሲሆን ጋብቻ መለኮታዊ ተቋም መሆኑን ገልፆ በትዳር ውስጥ ምን ምን ነገሮች ያስፈልጋሉ፤ ለትዳር መደፍረስ የሚያበቁ ችግሮችስ ምንድን ናቸው፤ ችግሮች ሲያጋጥሙ በምን መንገድ ችግሮቹን መፍታትና ማስቀጠል ይቻላል በሚሉት ላይ ጥናቶችን ካደረገ በኋላ መፅሀፉን እንደፃፈ ገልጿል፡፡ ለምርጥ ትዳር ወሳኝ የተባሉ ምስጢራት የተካተቱበት ነው የተባለው ይሄው መፅሀፍ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥናት እየተደረገበት እንደሚገኝም ደራሲው ገልጿል፡፡
በ176 ገፅ የተቀበበው መፅሀፉ በ299 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል፡፡ ደራሲና ዳይሬክተር ሱራፌል ኪዳኔ ከዚህ ቀደም በፊልሙ ኢንደስትሪ በርካታ ሥራዎችን የሰራ ሲሆን “ሹገር ማሚ”፤ “የተከለከለ”፤ “ሳሌት”፤ “ፍቅርና ፖለቲካ”፤ “ፍቅሬን ያያችሁ”ና ሌሎችንም ፊልሞች በማዘጋጀት ለእይታ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

Read 11886 times