Saturday, 12 November 2022 12:35

“የተዳፈነው ታሪክ” መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በገጣሚና ደራሲ በሁሉም አለበል የተሰናዳና በራስ ጉግሳ ወሌ ላይ የሚያጠነጥነው “የተዳፈነው ታሪክ” መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
መፅሀፉ በዋናነት ብዙ ስላልተነገረላቸውና ሥላልተዘመረላቸው ባለታሪክ ራስ ጉግሳ ወሌ፤ የትውልድ፤ የአስተዳደግና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የነበራቸው አስተዋፅኦ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ደራሲዋ ገልፃለች፡፡
በ201 ገፅ ተመጥኖ በ500 ብር ለገበያ የቀረበው መፅሀፉ በሁሉም መፅሀፍት መደብርና በአዟሪዎች እጅ እንደሚገኝም ታውቋል፡፡ ገጣሚና ደራሲ በሁሉም አለበል ከዚህ ቀደም “የሸንበቆ ባህር” እና “ሳምራዊ” የተሰኙ የግጥም መፅሀፍትን እንዲሁም “የተዋጡ ድምፆች” እና “ውስብስብ ውሎዎች” የተሰኙ የአጫጭር ልቦለድ ስብስብ መፅሀፍትንና በቀኝአዝማች ምስጋናው አዱኛ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነውን “ታሪክን በቅኔ” የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል፡፡  

Read 11684 times