Saturday, 12 November 2022 13:03

ናሽናል አቪዮሽን ዛሬ ኮሌጅ ተማሪዎችን ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባልና የናሽናል ኤርዌይለ እህት ኩባንያ የሆነው “ ናሽናል አቪዮሽን ኮሌጅ” ዛሬ ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) አዳራሽ ያስመርቃል፡፡
ኮሌጁ በተሰማራበት ከፍተኛ ትምህርት ስልጠና፤ በአቪዮሽን፤ በቱሪዝም፤ በሎጂስቲክስና በቢዝነስ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በማስተርስ፤ በዲግሪና በሰርተፍኬት እንደሚያስመርቅ ናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በምረቃ ስለሥርዓቱም ላይ የክህሎትና ሥራ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፤ የከፍተኛ ትምህርት ሀላፊዎች፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተወካዮች የተመራቂ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ ናሽናል አቪዮሽን ኮሌጅና ናሽናል ኤርዌይለን ጨምሮ ዘጠኝ የቢዝነስ ግሩፖችን አቅፎ የሚሰራና በከፍተኛ ካፒታል የተቋቋመ ትልቅ ኩባንያ መሆኑንና በአገር ኢኮኖሚና በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 11453 times