Friday, 04 November 2022 00:00

ክብር ለመከላከያ ሠራዊት - የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ መልዕክት

Written by 
Rate this item
(2 votes)

  “አንተ የተከበርከው፣ ለውድ ህይወትህ የማትሳሳ፣ ሁለት ወር ሙሉ በብርድ፣ በዝናብ በየጫካው የተኛህ አንተ የኢትዮጵያ ኩራት የአገር መከላከያ፤ አንተ የኢትዮጵያ ወኔ፤ አንተ የኢትዮጵያዊነት ምልክት፤ አንተ የጀግንነት ምልክት፤ በአንተ ድካም በአንተ መቁሰል በአንተ ህይወት ኢትዮጵያ ዳግም ቆማ በክብር መናገር ችላለች። መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ለአገር መከላከያ ያለንን ታላቅ አክብሮትና ፍቅር በታላቅ ትህትና እንድንገልጽ እጠይቃለሁ፡፡
“እናንተ ጀግኖች ሞታችሁ ሞት አይደለም ፤ የደማችሁ መፍሰስም የደም መፍሰስ አይደለም፤ የኢትዮጵያ መጽናት ነውና እንወዳችኋለን እናከብራችኋለን። ክብር ምስጋና ለተሰውት ሰማዕታት እንዲሆን፣ የተቀራችሁ ጀግኖች ክብር እንዲሰማችሁ ለመግለጽ እወዳለሁ፡”

Read 3144 times