Saturday, 05 November 2022 11:00

8ኛው የአፍሪካ ሶርሊንግና የፋሽን ሳምንት ተከፈተ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 8ኛው የአፍሪካ የሶርሲንግና የፋሽን ሳምንት ትላንት ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ረፋድ ላይ በስካይላይት ሆቴል ተከፈተ፡፡ እስከ ጥቅምት 28 ይቆያል በተባለው በዚህ የፋሽን ሳምንት በአፍሪካ ምርቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ የጥጥ፤ የጨርቃጨርቅ ፤የአልባሳት፤ የቆዳ፤ የቴክኖሎጂ፤ የቤት ማስጌጫ ኢንዱስትሪን ጨምሮ የጅምላና የችርቻሮ ሽያጭ፤ የቡቲክ ሱቆችንና የሆቴል ኢንዱስትሪውን ያካተተ በርካታ ትርኢት ይቀርብበታል ተብሏል፡፡
በዚህ የፋሽን ሳምንት የንግድ ትስስሩን ለማጠናከር ከጂአይዜድ (GIZ)፤ ከዮኤንአይዲኦ (UNIDO) እና መሰል የመንግስት እና የግብረሰናይ ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት ደረጃው ከፍ ያለ እንዲሆን ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡
ይህ የሶርሲንግና የፋሽን ሳምንት የተዘጋጀው “መሴ ፋራንክፈርት”፤ ከኢትዮጵያ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፤ ከኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማትና ኢንስቲትዮት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ቆዳና ልብስ ስፌት ማህበራት ፌደሬሽን ጋር በመተባበር መሆኑም ተገልጿል፡፡
አዘጋጁ በኬኒያ የሚገኘው የምስራቅ አፍሪካ ንግድና ባዛር ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ዋና መስሪያ ቤት ሲሆን ዋና መስሪያ ቤቱ በጀርመን አገር መሆኑንና የዓለም ትልልቅ ኩባንያዎችን በመወከል እስካሁን ከ250 በላይ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢቶችንና ባዛሮችን በአፍሪካ ውስጥ ማዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡
ይህ የሶርሲንግና የፋሽን ሳምንት በምስራቅና በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙ ከ30 በላይ ባለተሰጥኦ አፍሪካዊያን ዲዛይነሮችን ከዓለም አቀፍ ሸማቾች እና የፋሽን ብራንዶች ጋር በማገናኘት ወደፊት የተሻለ በመስራት አቅማቸውን የሚያሳዩበትን አጋጣሚም ይፈጥራል ተብሏል፡፡    

Read 11448 times