Saturday, 29 October 2022 12:33

የዓይን፣ የጆሮና የአዕምሮ ምስክር” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በደራሲ ወርቅዬ ደምሴ የተጻፈው “የዓይን፣ የጆሮና የአዕምሮ ምስክር” የተሰኘው በግብረገብና ስነምግባር ላይ አተኩሮ የተዘጋጀው  መጽሐፍ ለንባብ በቃ።
መጽሐፉ በሰው ልጅ አስተሳሰብና ማንነት ላይ ትኩረቱን አድርጎ፣ የሃገራችንን ጥንታዊና ሐይማኖታዊ የስነምግባር አስተምህሮን መሰረት በማድረግ፣ ባሁኑ ወቅት ያለውን የሐገራችንን ማህበራዊ ኑሮ ከዘመናዊው ዓለም ጋር እያነጻጸረ የሚያሳይ እንደሆነ ታውቋል፡፡  
“የዓይን፣ የጆሮና የአዕምሮ ምስክር” መጽሐፍ፣ ደራሲው ከትምህርትና ከረዥም ዘመን የስራ ልምድ ያገኙትን  ዕውቀት አቀናጅተው  ያሰናዱት  ነው ተብሏል።
መጽሐፉ 12 ምዕራፎችና 554 ገጾች ያሉት  ሲሆን፤ ዋጋው 250 ብር ነው፡፡
ደራሲው፣ በ1990 ዓ.ም “የፍቅር ጀርባው”  የተሰኘ ረጅም ልብ ወለድ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃታቸው ይታወቃል፡፡

Read 21180 times