Saturday, 29 October 2022 11:30

“በጦርነቱ የተሳተፉ ወገኖች በሙሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽመዋል” - አምነስቲ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተሳተፉ ወገኖች  በሙሉ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን  ፈጽመዋል አለ፡፡ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ ጥልቅ ምርመራ እንዲደረግም ጠይቋል፤ አምነስቲ፡፡  
በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያና ኤርትራ ተመራማሪ የሆኑት አቶ ፍስሃ ተክሌ፣ ባለፈው ረቡዕ  በናይሮቢ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
“ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ከጦር ወንጀልና በሰብዓዊነት ላይ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች ጋር የሚስተካከሉ  ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ተመልክተናል፡፡
ከሰነድናቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል አስገድዶ መድፈርና አስደንጋጭና ጭካኔ የተሞሉባቸው ጾታዊ ጥቃቶች ይገኙባቸዋል፡፡” ብለዋል፤ ተመራማሪው አቶ ፍስሃ ተክሌ፡፡
“እንደ አምነስቲ የሰነድናቸው የአስገድዶ መድፈርና የጾታ ጥቃቶች በጦርነቱ በተሳተፉ በሁሉም ወገኖች የተፈጸሙ ናቸው፡፡ በዚህ ጦርነት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ያልፈጸመ ማንም  ንጹህ ወገን የለም፡፡
ሁሉም ፈጽመዋል፡፡” ሲሉም አክለዋል፤ ተመራማሪው፡፡

Read 11141 times