Saturday, 20 October 2012 11:54

“የዐይን ፀጥታ” እና “የጦርነት ጥበብ” ለንባብ በቁ

Written by  መልካሙ ተክሌ melkamutekle@gmail.com
Rate this item
(1 Vote)

“ያመነም ያላመነም” ይመረቃል
በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ጥበባዊ ፅሁፎችን በማስነበብ የሚታወቀው ደራሲ ኪሩቤል ሳሙዔል “የዐይን ፀጥታ እና ሌሎች አጫጭር ነፍስ ወለዶች” የተሰኘ ጥበባዊ መፅሃፍ ለንባብ አበቃ፡፡
በ168 ገፆች የተቀነበበው መፅሃፉ፤ 24 ታሪኮችን የያዘ ሲሆን ዋጋው 30 ብር ነው፡፡
“The art of War” የተሰኘው የአሸናፊነትን ሥልት የሚያስተምረው መፅሃፍ “የጦርነት ጥበብ” በሚል ርእስ በፍቅሩ ሃይሌ ተተርጉሞ ሰሞኑን ለንባብ ቀረበ። በፋርኢስት ማተሚያ ቤት የታተመው 129 ገፆች ያሉት መፅሐፉ፤ በ30.50 ብር እየተሸጠ ነው።
በሌላም በኩል በግርማይ አብርሃ የተዘጋጀውና ባለፈው መንግስት ተፈፀመ ስለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚተርከው “ያመነም ያላመነም” መፅሐፍ ዛሬ ከሰዓት በኋላ መስቀል አደባባይ በሚገኘው የቀይሽብር ሰማዕታት ቤተመዘክር ከቀኑ 10 ሰዓት ይመረቃል፡፡

Read 1972 times Last modified on Saturday, 20 October 2012 12:03