Print this page
Saturday, 22 October 2022 17:09

“ኢትዮጵያ የተቃርኖ ምኩራብ” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በአሀዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ላለፉት አምስት ዓመታት “አሀዱ መድረክ” በሚል ድንቅ ዝግጅታቸው የምናውቃቸው የጋዜጠኛ ሊዲያ አበበና ጋዜጠኛ ሱራፌል ዘላለም የጋራ ስራ ሆነው “ኢትዮጵያ የተቃርኖ ምኩራብ” ቅፅ አንድ መፅሐፍ ለንባብ በቃ።
ጋዜጠኞቹ በአምስት አመቱ የአሀዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን የአሀዱ መድረክ ዝግጅታቸውን ወደ መፅሐፍ በመቀየር ፖለቲከኞችን ብቻ አካትተው ለንባብ ማብቃታቸውን ተናግረዋል። እንደ ጋዜጠኞቹ ገለጻ የአምስት ዓመቱን ፕሮግራም ወደ መፅሐፍ የቀየሩት በታሪክ ሰነድነት እንዲቀመጥ በማሰብ ነው። መጽሐፉ በዋናነት ይህ ሁሉ ተቃርኖ ኢትዮጵያን የመቀራመት ወይስ የማዳን ተልዕኮ ነው ሲል ይጠይቃል።
28 ፖለቲከኞችን ያካተተውና በወገግታ አታሚዎች ለህትመት ብርሃን የበቃው ይኸው መጽሐፍ በ200 ገፅ ተቀንብቦ በ350 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በቀጣይ ወደ ኦሮምኛ ተተርጉሞ ለንባብ እንደሚበቃም ጋዜጠኞቹ ገልጸዋል። ቅፅ ሁለት መፅሀፋቸው ደግሞ ፖለቲከኞችን፣ ምሁራንን የማህበረሰብ አንቂዎችንና ባለድርሻ አካላትን አካትቶ በቅርቡ ለንባብ እንደሚበቃ ጋዜጠኞቹ ሊዲያ አበበና ሱራፌል ዘላለም ጨምረው ገልጸዋል።

Read 20971 times