Saturday, 24 September 2022 17:22

የ22ኛው ዓለም ዋንጫ 32 አሰልጣኞችና ደሞዛቸው

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(2 votes)

 በኳታር የሚካሄደው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ሊጀመር ከ2 ወራት ያነሰ ግዜ ቀርቷል፡፡  በዓለም ዋንጫው የሚሳተፉ 32 አሰልጣኞች እና የሚያገኙት ዓመታዊ የደሞዝ ክፍያ በማጥናት ደረጃቸውን ይፋ ያደረገው ታዋቂው የስፖርት ፋይናንሻል ጉዳዮች ተንታኝ ፋይናንስ ፉትቦል ነው፡፡ የጀርመን ዋና አሰልጣኝ ሃንስ ዴይተር 6.5 ሚሊዮን ዩሮ ዓመታዊ ደሞዝ በማግኘት የመጀመርያውን ስፍራ ይዘዋል፡፡
የእንግሊዙ ጋሬዝ ሳውዝ ጌት በ5.8 ሚሊዮን ዩሮ፤ የፈረንሳዩ ዲዴየር ዴሻምፕ በ3.8 ሚሊዮን ዩሮ፤ የብራዚሉ ቲቴ በ3.6 ሚሊዮን ዩሮ እንዲሁም የሆላንዱ ሊውስ ቫንጋል 2.9 ሚሊዮን ዩሮ በማግኘት እስከ አምስተኛ ደረጃ አከታትለው ይወስዳሉ፡፡ ከ6 እስከ 32 ደረጃ ያላቸው የሚከተሉት ናቸው፡፡
6. ጌራርዶ ማርቲኖ (ሜክሲኮ) – €2,900,000
7. ሊዮኔል ሳኮልኒ (አርጀንቲና – €2,600,000
8. ፌልኪስ ሳንቼስ ባስ (ኳታር) – €2,400,000
9. ፈርናንዶ ሳንቶስ (ፖርቱጋል) – €2,250,000
10. ሙራት ያኪን (ስዊዘርላንድ) – €1,600,000
11. ፓውሎ ቤንቶ (ደቡብ ኮርያ) – €1,300,000
12. ግራሃም አርኖልድ (አውስትራሊያ) – €1,300,000
13. ግሬግ ቤልሃርተር (አሜሪካ) – €1,250,000
14. ሮበርቶ ማርቲኔዝ (ቤልጅዬም) – €1,200,000
15. ካስፐር ሂውልማንድ (ዴንማርክ) – €1,150,000
16. ሊውስ ኢነሪኬ (ስፔን) – €1,150,000
17. ሄርቬ ሬናርድ (ሳውዲ አረቢያ) – €1,100,000
18. ሃጂሜ ሞራይሱ (ጃፓን) – €1,050,000
19. ቫሂድ ሃሊሆድዚክ (ሞሮኮ) – €920,000
20. ዲዬጎ አሎንሶ (ኡራጋይ) – €860,000
21. ጉስታቮ ጄ አልፋሮ (ኢኳዶር) – €770,000
22. ድራጋን ስቶጆኮቪክ (ሰርቢያ) – €650,000
23. ድራጋን ስኮቺክ (ኢራን) – €650,000
24. ዝላትኮ ዳሊክ (ክሮሽያ) – €550,000
25. ቼዝላው ሚከኒዊዝ(ፖላንድ) – €500,000
26. ጆሃን ሃርድ ማን (ካናዳ) – €480,000
27. ክሪስ ሁገተን(ጋና) – €400,000
28. ሮብ ፔጅ (ዌልስ) – €380,000
29. ሊውስ ኤፍ ስዋሬዝ  (ኮስታሪካ) – €350,000
30. ሪጎበርት ሶንግ (ካሜሮን) – €340,000
31. አሊዊ ሲሴ  (ሴኔጋል) – €310,000
32. ጃሌል ካድሪ (ቱኒዚያ) – €130,000
በፋይናስ ፉትቦል ጥናት መሰረት በአፍሪካ እግር ኳስ በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ከፍተኛ ክፍያ የሚያገኙ ዋና አሰልጣኞች በዓለም ዋንጫ ላይ ከሚሳተፉ የአፍሪካ ብሄራዊ ቡድኖች የሚሰሩት አፍሪካውያን ናቸው፡፡ የካሜሮን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆነው ሪጎበርት ሶንግ በ340ሺ ዩሮ ዓመታዊ ደሞዝ የአፍሪካ ከፍተኛው ተከፋይ ነው፡፡ የሴኔጋሉ አሊዊ ሲሴ 310ሺ ዩሮ እንዲሁም የቱኒዚያው ጃሌል ካድሪ 130ሺ ዩሮ ዓመታዊ ደሞዝ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ይሰጣቸዋል፡፡ በአፍሪካ እግር ኳስ  ከዓለም ዋንጫ ውጭ  በተለይም በአፍሪካ ዋንጫና በአፍሪካ አገራት ሻምፒዮንሺፕ ቻን ውድድር ላይ የሚሰሩ  ብዙዎቹ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች ከአህጉሪቱ ውጭ የመጡ ሲሆን ከ5ሺ ዩሮ አንስቶ እስከ 108ሺ ዩሮ ዓመታዊ ደሞዝ የሚያገኙ ናቸው፡፡

Read 20933 times