Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 20 October 2012 10:08

ኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪ ሴቶች በዓለም አቀፍ ጉባኤ ይሳተፋሉ

Written by 
Rate this item
(6 votes)

በጋና መዲና አክራ ከጥቅምት 28 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት በሚካሄደው የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ዓለምአቀፍ ማህበር ጉባኤ ላይ በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የሚሠሩ አስራ ሁለት ኢትዮጵያውያን እንደሚካፈሉ ተገለፀ፡፡
የአባይ ባንክ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ እና የቡና ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ እሸቱ ፋንታዬ በ18ኛው የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ከሚሳተፉት የሚሳተፉ ሲሆን ከአዲስ አበባ እና ከክልል የተውጣጡ በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተሰማሩ ነጋዴዎችም በጉባኤው ይካፈላሉ፡፡ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ለአንድ አገር እድገት መሰረቶች ናቸው ያሉት የአባይ ባንክ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሰንበት፤ ተቋማቱ በጥቂት የሰው ሃይል አምራች እና አገልግሎት ሰጭ እንደሆኑ ጠቅሰው፤ ተቋማቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚታየው የስራ አጥነት ችግር መፍትሄ ናቸው ብለዋል፡፡

አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በተፈጥሯቸው ለየት ያለ የፖሊሲ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ያሉት ወይዘሮ መሰንበት፤ ተቋማቱ ወደ ትልቅ ኢንዱስትሪ ደረጃ እንዲያድጉ በፋይናንስ፤ በቴክኖሎጂ እና በአቅም ግንባታ በመደገፍ በተፎካካሪነት እንዲሰሩ መጠነ ሰፊ እገዛ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል፡፡ አባይ ባንክ ላለፉት በሁለት ዓመታት ሁለት አይነት መንገድ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን ለመደገፍ ሲሰራ መቆየቱን ይገልፃሉ፡፡ የመጀመርያው “አይድያ ፋይናንሲንግ” በሚል ለስራ ፈጣሪዎች ያለዋስትና በሃሳብ ብቻ ተመስርቶ ብድር የሚሰጥበት አሰራር ሲሆን ሌላው “ሊዝ ፋይናንሲንግ” በሚል ለስራቸው አስፈላጊ የሆኑ ማሽኖችና መሳሪያዎች በኪራይ መልክ እንዲጠቀሙና በስራቸው እድገት ካገኙ በኋላ የተከራዩዋቸውን ነገሮች ወደ ራሳቸው ንብረት እንዲለወጡ ለማገዝ የተዘረጋ አሰራር መሆኑን ፕሬዚዳንቷ ገልፀዋል፡፡
በጋና በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ የስራ ፈጠራ በሴቶች ላይ አተኩሮ ቢሰራበት ውጤት ያመጣል በሚለው ሃሳብ የጋራ መግባባት እንዲፈጠር ጥረት አደርጋለሁ ያሉት ወይዘሮ መሰንበት፤ መንግስታት ከሴቶች ጋር ቢሰሩ ለአገር እድገትና ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ገልፀዋል፡፡
ለአምስት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ ላይ ከ400 በላይ ሴት ስራ ፈጣሪዎች፣ ነጋዴዎች፣ ኢንቨስተሮች፣ የልማት መሪዎች፤ ማህበራዊ ስራ ፈጣሪዎች እና የሚዲያ ተቋማት ይሳተፋሉ፡፡ በጉባኤው ከአስር በላይ የፓናል ውይይቶችና 20 ዎርክሾፖች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ከእስያ፣ ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓ እና ከአሜሪካ የመጡ ስራ ፈጣሪ ሴቶች ምርቶች ለኤግዚቢሽን እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡
18ኛው የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ዓለምአቀፍ ማህበር ዓለም አቀፍ ጉባኤን “ዎርልድ አሶሴሽን ኦፍ ስሞል ኤንድ ሚድል ኢንተርፕራይዝስ” (WASEM) እንዳዘጋጀው ታውቋል፡፡
“women at 50’s age respect Events” የተሰኘ ፕሮግራም በዚሁ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ በይፋ ስራውን እንደሚጀምር ያስታወቁት የ”ዎርልድ ውመን ትሬድ ፌር አፍሪካ” የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ወ/ሮ መቅደስ መኩሪያ፤ 50ው ሴቷ የሥራና የእውቀት ልምድ የምታስተላልፍበት የመጀመሪያ ጊዜ እንጂ የመጨረሻው ያለመሆኑን ለማሳወቅ እንሰራለን ብለዋል፡፡
የ”ውመን አት 50” ፕሮጀክት ከአንድ ዓመት በፊት መጠንሰሱን የገለፁት ወይዘሮ መቅደስ፤ በመጪው የካቲት ወር በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን ፕሮግራም ለማካሄድ ከጋና ሴት ስራ ፈጣሪዎች ማህበር ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡ ፕሮግራሙ ለቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መታሰቢያ መደረጉን የጠቆሙት ዳይሬክተሯ፤ ጠ/ሚኒስትሩ ለአፍሪካ ሴቶች ህይወት መለወጥ ባበረከቱት የመሪነት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ከበሬታ መቀዳጀታቸውን አስታውሰዋል፡፡
“Women at 50’s” የዓለም ሴቶች ፕሮግራም እንደሚሆን የገለፁት ወ/ሮ መቅደስ፤ የአድማስ ኮሌጅ ም/ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አሰገች ወልደልዑል እንዲሁም የአዲስ አበባ እና የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤቶች ፕሬዚዳንቶች በፕሮጀክቱ ላይ በጋራ ለመስራት ፍላጐት አላቸው ብለዋል፡፡

 

Read 4147 times Last modified on Saturday, 20 October 2012 10:14