Saturday, 20 August 2022 12:50

በኢትዮጵያ ባለፉት ሳምንታት ግጭቶች በአንፃራዊነት ቀንሰዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

    ከሃምሌ 29 እስከ ነሀሴ 5 ቀን 2014 ዓ.ም በነበረው የአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የሃሪቱ አካባቢዎች በተከሰቱ 14 ያህል ግጭቶች፣ የ157 ሰዎች ህይወት ማለፉን የኢትዮጵያ የሰላም ሁኔታ ሳምንታዊ ግምገማ ሪፖርት ያመለክታል፡፡
ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ባደረገው እና ከ192 በላይ ሃገራትን የሠላም ሁኔታ በየጊዜው የሚከታተለው ACLED የተሰኘው ተቋም ይፋ ባደረገው የኢትዮጵያ ሳምንታዊ የሠላም ሁኔታ  ግምገማ ሪፖርቱ ካለፉት ጊዜያት አንጻር በሃገሪቱ ግጭቶች መቀነሳቸውን አመላክቷል፡፡
በሪፖርቱ መሰረት፤ ከሐምሌ 29 እስከ ነሀሴ 5 ባለው የአንድ ሳምንት ጊዜ በተከሰቱ 14 ግጭቶች 131 ጎራ ለይተው በግጭቱ የተሳተፉ ግለሰቦችን ጨምሮ፣ 26 በግጭቱ ተሳትፎ ያልነበራቸው ንፁሃን ተገድለዋል፡፡
ሠፊውን የግጭት መጠን የያዘው  የኦሮሚያ ክልል ሲሆን በመንግስት ሃይሎችና በሸኔ ታጣቂዎች መካከል በሳምንቱ 11 ያህል ጊዜ ግጭቶች ተፈጥረዋል ብሏል- ሪፖርቱ
ግጭቱ የተፈጠረባቸው አካባቢዎችም ቄለም ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉደሩ ወለጋ እና ኢሉባር ዞኖች እንዲሁም ምዕራብ ጎጂ እና ምዕራብ አርሲ ዞን ተጠቃሽ ሆነዋል፡፡
በግጭቱ ወቅት ከሞቱትና ከተገደሉት ንፁሃን ባሻገር በመቶዎች የሚቆጠሩ የአርሶ አድሮች መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች እና ንብረትም መውደማቸው ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ጋምቤላ አፋር እና ሶማሌ ክልል አዋሳኞችም በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በተፈጠሩ ግጭቶች የሰዎች ህይወት መጥፋቱ ተዘግቧል፡፡

Read 11207 times