Wednesday, 17 August 2022 20:20

ሌላ

Written by  ቢል - ዋስ
Rate this item
(1 Vote)

ከብርዳማው የክረምት ገላ የሚተነውን ቀዝቀዛ አየር ልከላ፣ ፍቅር ባስጌጣት ጎጆዬ፣ በውዴ እቅፍ ውስጥ መሽጌ ሳለሁ፣ እንዲህ አለችኝ ውዴ፡-
“አንተ ለእኔ ከሁሉም በላይ ነህ፡፡ የሚበልጥህ ይቅርና የሚስተካከልህ የለም፡፡ ብሩህ ራዕይን የምትፈነጥቅልኝ የእኔ ጸሃይ አንተ ነህ፡፡ እምነት አንተ፣ ፍቅርም አለኝታም ማለት አንተ እንጂ ሌላ ማን ሊሆን ይችላል?”
እኔም ደግሞ  እንዲህ አልኳት፤ ፍቅሬን፡፡ መፈታተንን ልፈታተናት፡፡
“እውን ውዴ ባንቺ ዘንድ የላቅሁ መሆኔ አያጠያይቅም?”
“በእርግጥ!” አለች ፍቅሬ፡፡
“ከእኔ የምታልቂው ከወዴትም የለ?”
“መች ተፈጥሮ”
“ጓደኛዬንም እንዲህ ነበር የምትለው” አልኳት፡፡
“ማንን?” አለች ውዴ፡፡
“አንቺ የማታውቂው አንድ ጓደኛዬን”
“ማናት? ምንስ ትለው ነበር?”
“ከእርሱ የሚልቅ አንድስ እንኳን እንደሌለ፡፡ ነገሩ እንኳን እውነት ነው፡፡”
“እንዴት?”
“እኛም እናምናለን”
“ምኑን?”
“እርሱ ከሁሉም እንደሚበልጥ”
“በምኑ?”
“በሁሉም ነገር፡፡ የሚስተካከለው አንድም የለም፡፡”
“እርግጠኛ ሆንክሳ”
“እውነቱ ይሄ ብቻ ስለሆነ ነው” አልኳት፡፡
“ታድላ! ግን አሁንም አብረው አሉ?”
“በፍጹም! ሳቁን ነጥቃው ሄዳለች” አልኳት፡፡
ከዚያም ውዴ በለዘበና የልመና ቃና ባለውድምጸት እንዲህ አለች፡-
“እባክህን አስተዋውቀኝ፡፡”
(አዲስ አድማስ ሐምሌ 7/ 1993 ዓ.ም)

Read 1200 times