Saturday, 06 August 2022 11:44

“ዱቡሻ” የኪነጥበብ ምሽት ዛሬ በሶዶ ከተማ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 ሁለተኛው ዙር  “ዱቡሻ” የኪነጥበብ ምሽት ዛሬ አመሻሹ ላይ በሶዶ ከተማ በጉተራ አዳራሽ በተለያዩ የኪነጥበብ መሰናዶዎች ይካሄዳል። በምሽቱ  ግጥም፣ ወግ በወላይትኛ፣ ሙዚቃ፣ የታዋቂ ሰዎች ልምድና ተሞክሮና ሌሎችም ዝግጅቶች  ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
በኪነጥበብ ምሽቱ ላይ ገጣሚያኑ መንበረማሪያም ሃይሉ፣ አስታውሰኝ ረጋሳ፣ ድምፃዊ ዘውዱ በቀለ፣ የሶዶ ከተማ ወጣት ገጣሚያንና ወግ አቅራቢዎች፣ የበኒ ማህበረሰብ ወጣት ሙዚቀኞች፣ በጉንጉን ባንድ ታጅበው ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ  የፕሮግራሙ አዘጋጅ ትዕግስት ታንቱ ገልፃለች።
በዚሁ ምሽት የፈንድቃ ባህል ማዕከል መሥራችና ባለቤት አርቲስት መላኩ በላይ በመድረክ ተገኝቶ ልምዱን ለታዳምያኑ ያካፍላል ተብሎ ይጠበቃል። “ዱቡሻ” በየሁለት ወሩ በሶዶና በሌሎች ከተሞች የሚካሄድ የኪነጥበብ መሰናዶ ነው።

Read 13008 times