“ህብረቱ ባደረገው ድጋፍ አማካኝነት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት፣ የክህሎት ማጐልበቻ እና እያደገ ለመጣው የሠራተኛ ኃይል የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ በመቻሉ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል” ብለዋል - አምባሳደር ማርሻል፡፡ Transformation Triggering Facility የተሰኘው የአውሮፓ ህብረት አዲሱ የልማት ድጋፍ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ መካከል የበለጠ ውጤታማ ትብብር ለማስፋፋት፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማሳደግ ያግዛል፡፡ በተጨማሪም ፕሮጀክቱ የአውሮፓ ህብረትና የኢትዮጵያ የቢዝነስ ትምህርት ቤትና የአነስተኛና መካከለኛ ተቋማት የፈጠራ ማበልፀጊያ ማዕከል ለመገንባት ያስችላል ተብሏል፡፡