በጥለት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን የተሰናዳው “ያልተከለሰ ያልተበረዘ” የተሰኘ የጥበብ ምሽት ሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በዕለቱም ገጣሚና ደሰራሲ በእውቀቱ ስዩም በአዳዲስ ግጥሞቹ፣ ወጎቹና ስታንዳፕ ኮሜዲ ስራው ታዳሚን እያዝናና ቁምነገር ሲያስጨብጥ እንደሚያመሽ አዘጋጁ “ጥለት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን” አስታውቋል፡፡
በምሽቱ ላይ ለመታደም መደበኛው ትኬት 300 ቪአይፒው 500 ብር መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ ትኬቶቹን በሁሉም የዳሽን ባንክ ቅርንጫፎችና በአሞሌ ማግኘት እንደሚቻል አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡