Saturday, 11 June 2022 19:49

“ሄሎ አዲስ” የሙዚቃ ድግስ ዛሬ በጊዮን ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ከሌቭል ዋን ኢንተርቴይመንት በጋራ ያዘጋጁትና አንጋፋና ወጣት ሙዚቀኞች የሚሳተፉበት “ሄሎ አዲስ” የሙዚቃ ድግስ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በጊዮን ሆቴል ይካሄዳል፡፡
ይህ የሙዚቃ ድግስ የተዘጋጀው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ የተመሰረተበትን 22ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሲሆን፣ በሀገራን የመጀመሪያው የሆነው ይህ ኤፍ ኤም ሬዲዮ የብዙዎችን ሙዚቀኞችን ስራ በመልቀቅ፣ በመተንተንና ሙዚቀኞችን በእንግድነት በመጋዝና በተለያየ መንገድ ሬዲዮ ጣቢያው ከሙዚቃ ጋር ያለውን ጥብቅ ቁርኝት ከምስረታ በዓሉ ጋር አገናኝቶ ትዝታን ለማስቀረት ታስቦ ስለመሆኑ የሬዲዮ ጣቢው ሀላፊዎች ሀሙስ ረፋድ በሸራተን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ተወዳጁ ፀሀዬ ዩሀንስ፣ አብዱ ኪያር፣ሳሚ ዳንና ቬሮኒካ አዳነ የሚያቀነቅኑበትና ለ4  ሰዓት ይቆያል በተባለው ድግስ ላይ ለመታደም መደበኛውን ትኬት ቀድመው ለሚገዙ 400 ብር፣ በር ላይ ለሚገዙ 500 ብር ቪአይፒው 1 ሺ500 ብር መሆኑም ተገልጿል፡፡
ህዝቡን በተገቢው መንገድ ለማዝናነት ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጋቸውንም ድምጻዊ አብዱ ኪያርና ሳሚ ዳን በመግለጫው ላይ አብራርተዋል፡፡


Read 11441 times