Sunday, 29 May 2022 00:00

በአለማችን ከ100 ሚ. በላይ ሰዎች ለመፈናቀል ተዳርገዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  በመላው አለም ግጭትና ጦርነትን ጨምሮ በተለያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሚሊዮን ማለፉንና ከእነዚህም መካከል 60 ሚሊዮን ያህሉ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መሆናቸውን ተመድ አስታውቋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በሳምንቱ መጀመሪያ  ይፋ ባደረገው አዲስ መረጃ እንዳለው፤ ከ14 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ያፈናቀለውን የዩክሬን ጦርነት ጨምሮ የተለያዩ የአለማችን አገራት ሰዎች ግጭት፣ ብጥብጥ፣ እስራት፣ ግድያና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በመሸሽ ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በ2012 የፈረንጆች አመት 41 ሚሊዮን የነበረው የአለማችን ተፈናቃዮች ቁጥር፣ በ2019 ላይ 79.5 ሚሊዮን፣ በ2020 ከ82 ሚሊዮን በላይ፣ በአሁኑ ወቅት ይህ ቁጥር ከ100 ሚሊዮን ማለፉንም የኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል፡፡

Read 1657 times