Saturday, 28 May 2022 13:41

“የባየሽ ማስታወሻ” መፅሐፍ ለአንባቢያን ቀርቧል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(3 votes)

 “የባየሽ ማስታወሻ ስድስት ወራት በአማፂያኑ ወረራ ወሎ፣ራያቆቦ” የተሰኘው የባዩዋ ሲሳይ የግል ማስታወሻ መፅሐፍ ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡
መፅሐፉ ራያ ቆቦ እና የወሎ አካባቢዎች በህወኃት ሃይሎች ወረራ ስር በነበሩት ወቅት ጻሃፊዋ በየቀኑ በማስታወሻ ደብተራቸው እየመዘገቡ ያሰፈሩትን የየእለት ማስታወሻዎች ያካተተ መሆኑ ታውቋል፡፡
የመፅሐፉ ደራሲ በጦርነት ሴት ልጃቸውን በህወኃት ሃይሎች በሞት የተነጠቁ ሲሆን በወቅቱ ያሳለፉትን የ6 ወራት ውጣ ውረድም በሠፊው የሚስቃኝ መፅሐፍ ነው፡፡
መፅሃፉ የወሎ ህብረት ባደረገው ድጋሚ የታተመ ሲሆን በ2 መቶ ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡




Read 21186 times