Saturday, 21 May 2022 10:51

ኢዜማ የጠቅላላ ጉባኤ ቀን እና የመሪ መምረጫ መመዘኛዎች ላይ ማሻሻያ አ ደረገ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

ቀጣይ መሪውን “በሠለጠነ መንገድ” ለመምረጥ እቅድ ያወጣው ኢዜማ፤ መሪውን የመምረጫ መስፈርት እና የጠቅላላ ጉባኤ ማካሄጃ ቀን ላይ ማሻሻያ አደረገ፡፡የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫው፤ ለመሪነት የሚወዳደሩ እጩዎች ምዝገባ  ማከናወኛ ጊዜን ጨምሮ የጠቅላላ ጉባኤ ማካሄጃ ቀኑን ከሰኔ 11 እና  12 ወደ ሰኔ 25 እና 26 ቀን 2014 ዓ.ም አራዝሟል፡፡በተቀመጡ መመዘኛ መስፈርቶች መሰረት ለመጨረሻ ዙር ውድድር  ተጣርተው የሚቀርቡ እጩዎች ብዛት ቀደም ብሎ ባወጣው መመሪያ ሦስት የነበረ ሲሆን በተሻሻለው መመሪያ አምስት ይሆናል ተብሏል፡፡ በመቶኛ ተሠልቶ በሚቀመጥ የመመዘኛ ነጥብ አሠጣጥ ላይም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተወሰኑ ማሻሻያዎች ማድረጉ ታውቋል፡፡በዚህ ማሻሻያ መሰረት የእጩዎች መቀበያ ጊዜ ከሚያዚያ 25 እስከ ግንቦት  16 ቀን 2014  እንዲሆን፣ እጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ የሚያከናውኑበት ጊዜ ከሰኔ 1 እስከ 24 እንዲሆንና የመጨረሻ ምርጫ የሚካሄድበት ቀን ሰኔ 26 ቀን 2014 መሆኑ ይታወቅልኝ ብሏል፤ ኢዜማ በመግለጫው፡፡


Read 10882 times