Saturday, 14 May 2022 00:00

ሰዎች ትልቅ ቦታ ሲደርሱ ደስ ይላል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 አዲስ አለማየሁ እና ሳምራዊት ፍቅሩ Rest of World (RoW) ዘንድሮ ባወጣው አመታዊ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ኢትዮጵያዊ ሆነዋል!
ይህ በአለም ዙርያ ያሉ እና ከካሊፎርኒያው ሲሊኮን ቫሊ ውጭ ያሉ 100 የቴክኖሎጂ ለውጥ አምጪ ሰዎች ዝርዝር በዘርፉ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተመርጠው የሚካተቱበት ሲሆን የ Kazana Group ሊቀመንበር አዲስ እና የ Ride መስራች ሳምራዊት ዘንድሮ ተጠቅሰዋል።
አዲስ አለማየሁ በዚህ ድርጅት ስር 16 ኩባንያዎችን የሚመራ ሲሆን የ251 ኮሚኒኬሽን እና የቃና ቲቪ መስራች አባል ነው፣ የአፍሮ ኤፍኤም ሬድዮ መስራችም ነበር። በአሁኑ ወቅት የ Albright Stonebridge Group ሲኒየር አማካሪ በመሆን እያገለገለም ይገኛል። ሳምራዊት ደግሞ Ride ድርጅትን መስርታ ለስኬት የበቃች ናት።
ሰዎች እንዲህ ትልልቅ ቦታ ደርሰው ሲገኙ ደስ ይላል፣ እንኳን ደስ አላችሁ።



Read 1463 times