በሌላም በኩል የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪ የሆነችው ውዳሴ ፈረደ ተገኘ “በራማ ሸለቆ” የተሰኘ የመጀመርያ የግጥም መፅሐፏን ለንባብ አበቃች፡፡ በ104 ገፆች የተካተቱት 108 ግጥሞች፤ ደራሲዋ ላለፉት አስር ዓመታት የፃፈቻቸው እንደሆኑ ታውቋው፡፡ ከብር በላይ ዋጋ አስከፍሎኛል ያለችው “አቤኔዘር የሕፃናት ማሳደጊያ” ሠራተኛ ውዳሴ ሁለት ሺህ ቅጂ ለማሳተም 21ሺህ ብር መክፈሏን ለአዲስ አድማስ ገልፃለች፡፡ በፋር ኢስት ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የታተመው መፅሐፍ፤ ለሀገር ውስጥ ገበያ በ25 ብር ለውጭ ገበያ ደግሞ በ10 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡