Saturday, 14 May 2022 00:00

“እኔማ እኔው ነኝ” ልብወለድ መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

 በመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ መምህርና በጎንደር ዩኒቨርስቲ የታሪክ ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ በሆነው ደራሲ ጁማሉልዲን ሚፍታህ አብደላ የተሰናዳውና በወጣቶች ህይወትና ስነ ልቦና ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተጻፈው “እኔማ እኔው ነኝ” የተሰኘ ልቦለድ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መፅሐፉ መቼቱን አዲስ አበባ፣መቀሌ መካነ ሰላምና ደሴ አድርጎ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባትን አንዲት ወጣት ማዕከል በማድረግ ከፆታዊ ጥቃት ጋር ተያይዞ የሚመጡ የስነ ልቦና ጫናዎችን ጨምሮ የህብረተሰቡን አመለካከትና በርካታ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነው ተብሏል፡፡
የአምስት ዓመት ታሪክን ማዕከል ያደረገው ይህ መፅሐፍ አንድ ታሪክ ወደ ኋላ አንድ ታሪክ አሁን ላይ እያደረገ የተፃፈና በርካታ ጉዳዮችን የሚዳስስ ሲሆን በ139 ገፅ ተቀንብቦ በ190 ብር ለገበያ መቅረቡንና በኤዞፕ መፃህፍት መደብርና በመፅሀፍ አዟሪዎች እጅ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 3047 times