Saturday, 06 October 2012 12:23

የሐረር ጅቦች በቀን ጥቃት ማድረስ ጀምረዋል

Written by  መታሰቢያ ካሣዬ
Rate this item
(3 votes)

ለዓመታት ከሰዎች ጋር ተላምደው በሠላም እንደኖሩ የሚነገርላቸው የሐረር ጅቦች፤ሰዎች ላይ በቀን ጥቃት ማድረስ እንደጀመሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ ሰሞኑን አራት ህፃናት ከመኖሪያ ቤታቸው ደጃፍ በጅቦች ሲወሰዱ የአካባቢው ህዝብ ተረባርቦ ሶስቱን ህፃናት በህይወት ሊያተርፋቸው ቢችልም  አንድ ህፃን በጅቡ ተበልቷል፡፡
በምሥራቅ ሐረርጌ ሐረር ዙሪያ አውራጃ፣ የሰንቂሴ ገበሬ ማህበር ሊቀመንበር አቶ አብዲ ሙሣ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ጅቦች በቀን ወደ ሰዎች መኖሪያ ቤት በመሄድ በተለይ ሕፃናት ልጆች ላይ ጥቃት ያደርሳሉ፡፡ ሁኔታው  እየከፋና ችግሩ እየተባባሰ ሲሄድ ለወረዳው ሪፖርት በማድረግ፣ የመከላከያ ጥይት እንዲሰጠንና ጅቦቹ ጥቃት ለማድረስ በሚመጡበት ጊዜ እርምጃ ለመውሰድ እንድንችል ጥያቄ ብናቀርብም ጥይት የለም የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል፡፡ ጅቦቹ በተለይ ጠዋት ከአንድ ሰዓት እስከ ሁለት ሰዓት ባለው ጊዜ ወደ ሰዎች መኖሪያ በመሄድ በህፃናትና በአቅመ ደካሞች ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው ብለዋል፡፡
በቅርቡ አራት ህፃናት በጅቦች መወሰዳቸውና ከእነዚህ መካከል የአካባቢው ሰው ባደረገው ርብርብ ሶስቱ ጉዳት ቢደርስባቸውም፣ ከሞት ተርፈው በህይወት ፋና እና በጆግላ  ሆስፒታሎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የተናገሩት ሊ/መንበሩ፤  የአንድ ህፃን ህይወት ማለፉን ገልፀዋል፡፡ የአካባቢው ህብረተሰብ በሁኔታው መደናገጥ በመፍጠሩና ችግሩ ዕለት ተዕለት እየተባባሰ በመሄዱ፣ ከዩኒቨርሲቲ በመጡ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች ድጋፍ፣ ያረጁና ህመምተኛ በጐችን እያረዱ ስጋቸውን በመርዝ በመለወስ ለጅቦቹ እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑን፣ በዚህ ዘዴም 21 የሚሆኑ ጅቦች መገደላቸውን አቶ አብዲ ገልፀዋል፡፡

ለዓመታት ከሰዎች ጋር ተላምደው በሠላም እንደኖሩ የሚነገርላቸው የሐረር ጅቦች፤ሰዎች ላይ በቀን ጥቃት ማድረስ እንደጀመሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ ሰሞኑን አራት ህፃናት ከመኖሪያ ቤታቸው ደጃፍ በጅቦች ሲወሰዱ የአካባቢው ህዝብ ተረባርቦ ሶስቱን ህፃናት በህይወት ሊያተርፋቸው ቢችልም  አንድ ህፃን በጅቡ ተበልቷል፡፡ በምሥራቅ ሐረርጌ ሐረር ዙሪያ አውራጃ፣ የሰንቂሴ ገበሬ ማህበር ሊቀመንበር አቶ አብዲ ሙሣ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ጅቦች በቀን ወደ ሰዎች መኖሪያ ቤት በመሄድ በተለይ ሕፃናት ልጆች ላይ ጥቃት ያደርሳሉ፡፡

ሁኔታው  እየከፋና ችግሩ እየተባባሰ ሲሄድ ለወረዳው ሪፖርት በማድረግ፣ የመከላከያ ጥይት እንዲሰጠንና ጅቦቹ ጥቃት ለማድረስ በሚመጡበት ጊዜ እርምጃ ለመውሰድ እንድንችል ጥያቄ ብናቀርብም ጥይት የለም የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል፡፡ ጅቦቹ በተለይ ጠዋት ከአንድ ሰዓት እስከ ሁለት ሰዓት ባለው ጊዜ ወደ ሰዎች መኖሪያ በመሄድ በህፃናትና በአቅመ ደካሞች ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው ብለዋል፡፡

በቅርቡ አራት ህፃናት በጅቦች መወሰዳቸውና ከእነዚህ መካከል የአካባቢው ሰው ባደረገው ርብርብ ሶስቱ ጉዳት ቢደርስባቸውም፣ ከሞት ተርፈው በህይወት ፋና እና በጆግላ  ሆስፒታሎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የተናገሩት ሊ/መንበሩ፤  የአንድ ህፃን ህይወት ማለፉን ገልፀዋል፡፡ የአካባቢው ህብረተሰብ በሁኔታው መደናገጥ በመፍጠሩና ችግሩ ዕለት ተዕለት እየተባባሰ በመሄዱ፣ ከዩኒቨርሲቲ በመጡ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች ድጋፍ፣ ያረጁና ህመምተኛ በጐችን እያረዱ ስጋቸውን በመርዝ በመለወስ ለጅቦቹ እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑን፣ በዚህ ዘዴም 21 የሚሆኑ ጅቦች መገደላቸውን አቶ አብዲ ገልፀዋል፡፡

Read 3701 times Last modified on Saturday, 06 October 2012 12:26