Saturday, 06 October 2012 11:55

“ለአቡነ ጳውሎስ” ሽልማት ተበረከተ

Written by  መልካሙ ተክሌ melkamutekle@gmail.com
Rate this item
(1 Vote)

 

ባለፈው ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ በኢየሩሳሌም የዕውቅና ሰርቲፊኬት ተበረከተላቸው፡፡
የመካከለኛው ምስራቅ ሰላምን አስመልክቶ እስራኤል ውስጥ ባደረጓቸው ንግግሮች ለእውቅናው የበቁት አቡነ ጳውሎስን የሸለመው በኢየሩሳሌም የሚገኘው All Nations Convocation Jerusalem የተሰኘ ድርጅት ነው፡፡
ከሳምንት በፊት በተካሄደው የሽልማት ሥነሥርዓት የፓርላማ አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳና የፓርላማ አባል ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስን ጨምሮ ከ180 ሀገራት የተውጣጡ ከፍተኛ ልዑካን ተገኝተዋል፡፡
በኪንግ ዴቪድ ሆቴል ሽልማቱን የተቀበሉት በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ናቸው፡፡

ባለፈው ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ በኢየሩሳሌም የዕውቅና ሰርቲፊኬት ተበረከተላቸው፡፡ የመካከለኛው ምስራቅ ሰላምን አስመልክቶ እስራኤል ውስጥ ባደረጓቸው ንግግሮች ለእውቅናው የበቁት አቡነ ጳውሎስን የሸለመው በኢየሩሳሌም የሚገኘው All Nations Convocation Jerusalem የተሰኘ ድርጅት ነው፡፡ ከሳምንት በፊት በተካሄደው የሽልማት ሥነሥርዓት የፓርላማ አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳና የፓርላማ አባል ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስን ጨምሮ ከ180 ሀገራት የተውጣጡ ከፍተኛ ልዑካን ተገኝተዋል፡፡ በኪንግ ዴቪድ ሆቴል ሽልማቱን የተቀበሉት በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ናቸው፡፡

 

Read 3058 times Last modified on Saturday, 06 October 2012 12:00