Saturday, 26 March 2022 10:52

“ገረገራ” ረዥም ልብወለድ መጽሐፍ እየተሸጠ ነው

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   የታደሰ አያሌው ድርሰት የሆነው “ገረገራ” የተሰኘው ረዥም ልብወለድ መፅሐፍ ባለፈው ሳምንት ለገበያ መቅረቡን ደራሲው ለአዲስ አድማስ ገልጿል።
“አንዲት ሙዚቀኛም ዶክተርም የስለላ ወኪልም የሆነች ቆንጆ ወጣት፣ የነርቭ ክፍተት ኖሮባት ከተወለደች ልጇ ጋር የምታየውን ከፍ-ዝቅ የሚተርክ መጽሐፍ ነው” ያለው ደራሲው፤ “ድርሰተ-ሰቦቹ እና መቼቱ ተምሳሌታዊ ሲሆኑ፣ አቀራረቡ ደግሞ ልብ አንጠልጣይ ነው” ብሏል።
በ244 ገጾች የተቀነበበው “ገረገራ” ልብወለድ መፅሐፍ፤ በ180 ብር እየተሸጠ ነው።
ደራሲው በ2011 ዓ.ም ለንባብ ያበቃው “ረበናት” የተሰኘ ስለላ ነክ ልብወለድ መጽሐፍ ሦስተኛ እትም በገበያ ላይ ሲሆን “ሸምጋይ” የተሰኘ ቴአትር በብሔራዊ ቴአትር ለማቅረብ ወረፋ እየጠበቀ መሆኑን ደራሲው ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡  

Read 11828 times