Saturday, 05 March 2022 12:07

“ኬሚስትሪ ክሮስወርድ ፐዝል” መፅሀፍ ዛሬ ይመራቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  በመምህር አዴው ዘሪሁን የተሰናዳውና ልጆች በቀላሉና በጨዋታ መልክ ኬሚስትሪን እንዲያውቁ የሚያስችለው “Chemistry CrossWord Puzzle” የተሰኘው መፅሀፍ ዛሬ ከረፋዱ 3፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ በብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡ መምህር አዴው ዘሪሁን አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ከኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በኬሚስትሪ፣ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኬሚካል ምህንድስና እንዲሁም ከኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተመርቋል፡፡
ከ1992 እስከ 2008 ዓ.ም በተለያዩ ት/ቤቶች በመምህርነት፣ በዩኒት መሪነት፣ በሱፐር ቫይዘርነትና በዳይሬክተርነት ከማገልገሉም በተጨማሪ በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ በኬሚካል ኢንጂነሪንግ ክፍል በላብራቶሪ ባለሙያነት አገልግሏል፡፡ በደረሰበት የመኪና አደጋ ቆሞ መራመድ አቅቶት የዊልቸር ተጠቃሚ የሆነውና ከዚህ ጋር በተያየዘ ባጋጠመው የኩላሊት ህመም ዲያሊስስ እያደረገ የሚገኘው ይሄው እንቁ መምህር ከህመሙ ጋር እየታገለም ቢሆን ልጆችን የሚያንጽ ነገር ከመስራት ባለመቦዘን በዊልቸር ላይ እያለ መፅፉን መፃፉንና ያስተምርበት የነበረው ት/ቤት መፅሐፉን እንዳሳተመለት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዛሬ በሚመረቀው የመምህር አዴው መፅሀፍ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተማሪዎቹ፣ መምህራን ጓደኞቹ፣ ትምህርት ላይ የሚሰሩ ተቋማት፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚታደሙ ሲሆን በመፅሀፉ ላይ ውይይት እንደሚደረግም ታውቋል፡፡

Read 11616 times