Saturday, 19 February 2022 12:38

በነዳጅ አቅርቦት ችግር ለሳምንት ምርቱን ያቋረጠውየፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ዳግም ስራ መጀመሩን አስታወቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   በነዳጅ አቅርቦት ችግር ሳቢያ ለአንድ ሳምንት ማምረት አቋርጦ የነበረው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ፤ ዳግም ሥራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡
የሸኔ ታጣቂ በፋብሪካው ላይ ጉዳት አድርሶበታል በሚል የተናፈሰው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው ብሏል፤ኮርፖሬሽኑ፡፡
በአሁኑ ወቅት በዓመት 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል ስኳርና 20 ሚሊየን ሊትር ኢታኖል የማምረት አቅም ያለው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ፤ በነዳጅ እጥረት ምክንያት ለአንድ ሳምንት ማምረት አቁሞ እንደነበር ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ባወጣው መግለጫ፤የነዳጅ ጫኝ መኪና አሽከርካሪዎች ለደህንነታቸው በመስጋት ወደ አካባቢው ለመሄድ ባለመፍቀዳቸው ከየካቲት 2  ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ምርት ለማቆም ተገዶ ነበር ብሏል፡፡
ሆኖም አሁን የነዳጅ አቅርቦት ችግሩ በመስተካከሉ ወደ መደበኛ የማምረት ስራው መመለሱ ተገልጿል፡፡
“በአካባቢው የሸኔ ታጣቂ በመግባት በፋብሪካው ላይ ጉዳት አድርሷል” የሚለው መረጃ አሉቧልታ መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፤ ከየካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መደበኛ የማምረት ስራው መግባቱን አመልክቷል፡፡
ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ ስኳር ማምረት የጀመረው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ፤ እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ ብቸኛው የኢታኖል አምራች ሆኖ የቆየ ግዙፍ ፋብሪካ መሆኑን፣ ኢዜአ በዘገባው አመልክቷል፡፡ ፡

Read 2461 times