Saturday, 12 February 2022 12:24

የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት የዕጩዎችን ጥቆማ መቀበል ጀመረ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  ዘንድሮ 10ኛ ዓመቱን የደፈነው የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት 10ኛ ዙሩን ሽልማት ለማካሄድ ከየካቲት 4 ቀን ጀምሮ የእጩዎችን ጥቆማ መቀበል መጀመሩን አስታወቀ። የሽልማት ድርጅቱ ከትላንት በስቲያ በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው ለዘንድሮው ሽልማት እንደተለመደው በ10ሩ ዘርፎች ማለትም በመምህርነት፣ በሳይንስ፣ በኪነጥበብ፣ በበጎ አድራጎት፣ በቢዝነስና ስራ ፈጠራ፣ በመንግስታዊ ተቋም ሃላፊነት መወጣት፣ በባህልና ቅርስ፣ በማህበራዊ ጥናት፣ በሚዲያና ጋዜጠኝነት እንዲሁም ለኢትዮጵያ እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዘርፎች  እጩዎች መጠቆም እንደሚቻል የገለፀው ድርጅቱ ጥቆማው እስከ መጋቢት 3  ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚቆይም አስታውቋል። ዘንድሮ በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ትከረት የሚያገኘው የፊልም ዳይሬክተርነት (የስነ-ርዕይ መሪነት) እንደሆነ የጠቆመው የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት  ይህም  “የፊልም እግዜሩ ዳይሬክተሩ” እንዲሉ ዋናው የፊልም የጀርባ አጥንት ዳይሬክተሩ በመሆኑ ነው ተብሏል።
ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት የሽልማቱን ፋይዳና ዓላማ በመገንዘብ ህዝብ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና ያቀረበው ድርጅቱ አሁንም ይሄው የህዝብ ድጋፍ እንዳይለየው ጠይቋል። እስከ መጋቢት 3 በሚቆየው የእጩዎች ጥቆማ ህዝቡ ለሀገርና ለወገን በ10ሩ ዘርፎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል ብሎ የሚያምንባቸውን በጎዎች በ0977-232323 በቴሌግራም፣ በዋትስአፕና This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.   እዲሁም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 150035 መጠቆም እደሚችል ተገልጿል።

Read 20023 times