Monday, 07 February 2022 00:00

“ያለፍኩትን ስቃኝ ከሀረርጌ ማልዶ እስከ ባህር ማዶ” መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

እድሜያቸው ወደ 80 ዓመት የተጠጋውና ሀገራቸውን በተለያዩ ሃላፊነቶች ያገለገሉት ደራሲ ፍሰሀ ተከስተ ያሰናዱት “ያለፍኩትን ስቃኝ ከሀረርጌ ማልዶ እስከ ባህር ማዶ” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ። ደራሲው ከልጅነት አስተዳደጋቸው፣ እስከ ትምህርት ዝግጅታቸው፣ ሀገራቸውን በተለያዩ ሃፊነቶች ባገለገሉበት ጊዜ ስለገጠማቸው ውጣ ውረድ፣ ስለመምህርነትና ሌሎች ሙያዎቻቸው፣ በውጪ ሀገር ስለነበራቸው የስራና የትምህርት ሁኔታ፣ ከሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት እስከ ኢህአዴግ ዘመን ያዩአቸውንና የታዘቧቸውን ሀገራዊ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸውን ሳይቀር የተነተኑበትና ለሌሎችም መማሪያ የሚሆን መጽሀፍ ነው ተብሏል።
ደራሲው ፍሰሃ ተከስተ በትምህርት ጥራት ችግሮችና መፍትሄዎቻቸውም ዙሪያ የታዘቡትንና የሚያውቁትን አስፍረዋል። በ16 ምዕራፍ ተከፋፍሎ በ240 ገጽ በተቀነበበው በዚህ መጽሐፍ የትምህርት ዝግጅትን ጨምሮ በርካታ የፎቶ ማስረጃዎችም የተካተቱ ሲሆን፣ በ150 ብርና በ15 ዶላር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል።

Read 28044 times