Sunday, 06 February 2022 00:00

“ሀገር ምን ትሻለች 4” ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን የተዘጋጀው “ሀገር ምን ትሻለች 4” የኪነጥበብ ምሽት የፊታችን ሰኞ ጥር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሄራዊ ቴአትር ይካሄዳል።
በዚህ ምሽት ዲስኩር፣ ወግ ግጥምና ሙዚቃ ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን፣ የተከበሩ ሙአዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ አበባው አያሌው (ረ/ፕ)፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር)፣ እና ገዛኸኝ ፀጋው (ዶ/ር)  ዲስኩር  የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ገጣሚያኑ ኤፍሬም ስዩም፣ ዘቢብ መልኬና ሰጥአርጌ አስማረ ግጥም እንዲሁም ህፃን አሜን ካሳሁን መነባንብ እንደሚያቀርቡ ታውቋል።
ሻሎም ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ባንድ ከድምጻዊያን ጋር ለታዳሚ ሙዚቃ የሚያቀርብ ሲሆን የመግቢያ ዋጋው 100 ብር እንደሆነና የመግቢያ ትኬቶቹም በጃዕፈር፣ አይናለምና ዮናስ መጽሐፍት መደብሮች እንዲሁም በጣይቱ ሆቴልና ከዛንቺስ በሚገኘው ጆሲ ልስብ ስፌት ቤት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።


Read 10646 times