Print this page
Saturday, 05 February 2022 12:01

“ሳንወድ እንገንጠል” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በሙያው ሲቪል መሃንዲስ በሆነውና ነፍሱ ለስነ-ጽሁፍ በምታደላው ደራሲ ሀናንያ መሃመድ (ካ) የተዘጋጀው “ሳንወድ እንገንጠል” የተሰኘ አዲስ የወግ ስብስብ መጽሐፍ ለንባብ በቃ። መጽሐፉ በዋናነት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የሆኑ ተጨባጭ የሀገራችን ሁኔታዎች በወግ መልክ የቀረቡበት ስለመሆኑ ደራሲ ሃናንያ መሃመድ (ካ) ገልጿል። በዚህ መጽሐፍ ሰባት ወጎች የቀረቡ ሲሆን፣ “ሸልሸላ”፣ “ሳንወድ እንገንጠል”፣ “ሳንወድ እንደመር”፣ “መካነ በዓላት”፣ “የተዘነጉ አጽሞች”፣ “ግራጫ ጦርነት”፣ “ቡልተካ” “የእምነት ልዩነት ያልበገራቸው ህዝቦች በትግራይ ሰንአፈ” እና “አፋርና ስደት “ የተሰኙ ወጎች መካተታቸውም ታውቋል። መጽሐፉ በ140 ገፅ ተቀንብቦ በ280 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል። ደራሲው ከዚህ ቀደም “ካ”፣ “እውነት ሲኮረኮም” (የግጥም ሲዲ)፣ እና “ሞቼ ነጻ ልውጣ” የተሰኙ መጽሐፍትን ለአንባቢያን ማቅረቡ አይዘነጋም።

Read 1810 times