በአብርሃም ግዛው ኢንተርቴመንትና የፕሬስ ስራዎች ድርጅት የተሰናዳው “ኢትዮጵያዊት” የተሰኘ የፋሽን ትርኢት ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ከኤድናሞል ወረድ ብሎ በሚገኘው “ዘ ባንክ ላይፍ ስታይል ላውንጅ” ይካሄዳል፡፡
በእለቱም በርካታ ስመጥርና እውቅ ዲዛይነሮች እና ሞዴሎች ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከፋሽን ትርኢቱ በተጨማሪም በጦርነቱ ለተጎዱና ለተፈናቀሉ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብርና ልዩ ልዩ መዝናኛዎች ለታዳሚ እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡ የመግቢያው ዋጋው 200 ብር መሆኑንም ጋዜጠኛ አብርሃም ግዛው ገልጿል፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና