በቅርቡ ስልጣናቸውን የለቀቁት የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ መርኬል፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ የቀረበላቸውን የተመድ ከፍተኛ አማካሪ ቡድን ሊቀ-መንበርነት ሹመት አልቀበልም ማለታቸውን ደችዌሌ ዘግቧል፡፡
አንቶኒዮ ጉቴሬስ ባለፈው ሳምንት የተመድ አለማቀፍ የሸቀጦች ጉዳይ ከፍተኛ አማካሪ ቡድን ሊቀ መንበር ሆነው እንዲሰሩ ለአንጌላ መርኬል ጥሪ ማቅረባቸውን ያስታወሰው ዘገባው፣ መርኬል ግን ለሹመት በመታጨታቸው ምስጋናቸውን በማቅረብ በግል ምክንያት የተነሳ ሹመቱን እንደማይቀበሉ ማስታወቃቸውን ነው ያመለከተው፡፡
ላለፉት 16 አመታት የጀርመን መራሂተ መንግስት ሆነው ያገለገሉትና ከወራት በፊት ከሃላፊነታቸው የለቀቁት የ67 አመቷ አንጌላ መርኬል የጠቆመው ዘገባው፣ መርኬል ፖለቲካውን እርም ቢሉም በቀጣይ የጡረታ ዘመናቸውን በምን ለመግፋት እንዳሰቡ እስካሁን ምንም ፍንጭ አመለስጠታቸውን ገልጧል፡፡
Published in
ከአለም ዙሪያ
Latest from Administrator
- German spying: Two suspected spies arrested in avaria
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’